ሁለቱ ሀገራት ሰላማዊ ግንኙነታቸዉን ለመመለስ ተስማምተዋል፡፡
በቤጂንግ ከተደረገው የጋራ ንግግር በኋላ ሁለቱ አገራት ግንኙነታቸዉን ለመመለስ መስማማታቸዉ ነዉ የተገለጸዉ፡፡
ሁለቱ አገራት ግንኙነታቸዉን ቀድሞ ወደ ነበረበት የትብብርና በጋራ የመስራት ሁኔታ ለመመለስ እና በሁለት ወራት ጊዜ ዉስጥም ኤምባሲዎችን ለመክፈት መስማማታቸዉን የኢራን ብሄራዊ ሚዲያን ጠቅሶ አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
በሁለቱ አገራት መካከል የነበረዉ ግንኙነት ኢራናዊ የሺያ እስልምና እምነት ተከታይ ግለሰብ በሳዑዲ አረቢያ ከተገደለ ከ2016 በኋላ መቋረጡ የሚታወስ ነዉ፡፡
ከዛን ጊዜ ጀምሮም የትኛዉም የሳዑዲ አረቢያ ዲፕሎማሲያዊ ተልዕኮ በኢራን ጥቃት ይደርስበት እንደነበርም ይወሳል፡
አሁን ላይ ሁለቱ ሃገራት አብሮነት ይሻለናል ብለዋል፡፡
ይህ የሳውዲ አረቢያ ውሳኔ ኢራንን እንደ ባላንጣ ለምትመከተው አሜሪካ መልካም ዜና እንዳልሆነም እየተነገረ ነው፡፡
የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ የነዳጅ እጥረት እንዳይፈጠር በሚል ሳውዲ ለሽያጭ የምታቀርበውን የነዳጅ መጠን እንድትጨምር በአሜሪካ ተጠይቃ ነበር፤ሳውዲ ግን ጥያቄውን ውድቅ አደረገችው፡፡
ከዛ ወዲህ በአሜሪካና ሳውዲ መካከል መጠነኛ ቅራኔ እንደተፈጠረ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
የኢራን-ሳውዲ ግንኙነት መጠናከር ደግሞ ሳውዲ ከአሜሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት ይበልጥ ሊዳው ይችላል ተብሏል፡፡
በእስከዳር ግርማ
የካቲት 01 ቀን 2015 ዓ.ም
Source: Link to the Post