ኢራን ለማንኛዉም ጥቃት አጸፋዊ እርምጃ ለዉሰድ ዝግጁ መሆኗን አስታወቀች፡፡የኢራኑ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ሬይሲ አገራችዉ ለማንኛዉም የጥቃት እርምጃ ዝግጁ እንደሆነች ተናግረዋል፡፡ፕሬዝዳንት…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/dYJkpe_9SRhepsyc4yyAGStt55mEUe2UNWAAH5M0WiEVwDxwpMNl72yucZNB545ZBt3rKTkfTczG7NcxTzsb4L6uT7y4vPh82QjsmRSvpySs67phUZ-hZfE9l7pF5DqtV2lXVecuyOxCRR13mUcpETEk7e24Wr2vSXN_k0UwojUwMnIC5M8JKXHGc-rnnYXkjdD8nW_LU-Xc1ZydF1UqoFzIVt2TzzbI2vYjlFt6HQPaHgIe0rZ6MLZzBCYa-l9KqbTtdBr7gvEEKGMsXBCLnCwYM_up7MihMYlxNzQyLaBwYnrxJ3WCIVOuGu9e3IgIZtwUPdW2c_DBnmrfFkqh4A.jpg

ኢራን ለማንኛዉም ጥቃት አጸፋዊ እርምጃ ለዉሰድ ዝግጁ መሆኗን አስታወቀች፡፡

የኢራኑ ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ሬይሲ አገራችዉ ለማንኛዉም የጥቃት እርምጃ ዝግጁ እንደሆነች ተናግረዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ሬይሲ ከታጣቂ ሃይሎች በአገራቸዉ ላይ ለሚፈጸም ማንኛዉም ጥቃት ጨካኝ ምላሽ እንደሚሰጡ አስጠንቅቀዋል፡፡

የኢራን መንግስት በሚወስደዉ አጸፋዊ እርምጃም ወራሪዎች በድርጊታቸዉ እንደሚጸጸቱ ተናግረዋል፡፡
ሬይሲ ይህን ያሉት በምእራብ ሃማዳን ግዛት የኢራንን ጦር በጎበኙበት ወቅት ነዉ፡፡
በእስላማዊዉ ኢራን ሃይል ፊት ማንም ሰዉ በሃገሪቱ መሬት ላይ ጥቃት ለመሰንዘር ማሰብ እንደደሌለበትም ነዉ ፕሬዝዳንቱ ያስጠነቀቁት፡፡

የኢራን መንግስት ባለዉ ጥንካሬ ኩራት እንደሚሰማቸም ነዉ ሬይሲ የተናገሩት፡፡
በተጨማሪም የኢራን የባህር ሃይል አዛዥ ጠላቶች አገሪቷ ላይ በማንኛዉንም የጥቃት እርምጃ ቢወስዱ አሳዛኝ ትምህርት እንደሚሰጡ ማስጠንቀቃቸዉን ፕሬስ ቴሌቪዠን ዘግቧል፡፡

በቤዛዊት አራጌ
ሐምሌ 22 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply