ኢራን በተቃዋሚ ሰልፈኞች ላይ ሰብዓዊ ወንጀል ፈፅማለች ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢራን ባለስልጣናት በሰላማዊ ሰልፎች ላይ ግድያ፣ማሰቃየት፣አስገድዶ መድፈርና ሌሎች ወንጀሎችን ፈፅመዋል ሲል አረጋግጧል።

ቴህራን በሰላማዊ ሰልፎች ላይ የወሰደችዉ የሃይል እርምጃ እና በሴቶች ላይ የሚደርሰዉ መድሎ ከፍተኛ የመብት ጥሰተን አስከትሏል ተብሏል።

በኢራን በመስከረም 2022 በተደረገ ሰልፍ የ22 ዓመት ኢራናዊት ወጣት የአለባበስ ህግን ጥሳለች በሚል ከታሰረች በኃላ ህይወቷ ማለፉ ይታወሳል።

በዚህም በተነሳ ቁጣ ለተከታታይ ሳምንታት በቴህራን ሰልፎች ተካሂደዋል።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የመጀመሪያ ዘገባ በኢራን ፆታዊ ጥቃት፣እስር እና እንግልት ተፈፅሟል ሲል ትላንት ባወጣዉ ሪፖርት አስታዉቋል።
ዘገባዉ የአልጀዚራ ነዉ

በእሌኒ ግዛቸው

የካቲት 30 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply