በቴክኒክ እና በሌሎች የዘርፉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎቿን አጠናቀዋል ያሉት እነኚህ ባለሙያዎች፣ የኒውክለር ቦንቡን ለማምረት የፖለቲከኞች ውሳኔ ብቻ እየተጠበቀ እንደሚገኝም አመላክተዋል፡፡
ከማል ካራዚ የተባሉት የሃገሪቱ ከፍተኛ የደህንነት አማካሪ ሃገሪቱ በጥቂት ቀናት ዩራኒየም የማበልፀግ አቅሟ ወደ 60 ከመቶ መድረስ መቻሉን አስታዉሰዋል፡፡
በቀጣይም 90 ከመቶ ለማድረስ ከፍተኛ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ፍንጭ ሰጥተዋል፡፡
የባይደንን ጉብኝት ተከትሎ ይህንን አስተያየት የሰጡት ከማል ካራዚ፣ ኢራን ሃገራቸው የፖለቲከኞቿ ውሳኔን ማጣቷ እንጂ ኒውክለርን ለመታጠቅ እሩቅ ሆና አይደለም ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ከሰሞኑ አሜሪካ እና እስራኤል በሃይልም ቢሆን የኢራንን የማብላያ አቅም ለመስበር እያቀዱ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
Source: Link to the Post