ኢራን እስራኤልን ደግፋ ንጹሃንን እያስጨረሰች ያለችዉ አሜሪካ ሌሎችን ለመክሰስ የሚያስችል ሞራል የላትም አለች

ቴህራን እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ የዘር ማጥፋት ጦርነት እየፈጸመች ነው ለዚህ ተግባር ተባባሪ የሆነችው ዋሽንግተን ነች ስትል ከሳለች፡፡

በአለም አቀፉ ማህበረሰብ የጠላቸዉ አሜሪካ በቴህራን ላይ ክስ የማቅረብ ምንም አይነት ምክንያት እንደሌላትም ገልፃለች፡፡

የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ናስር ካናኒ ፔንታጎን በህንድ ውቅያኖስ ውስጥ ሲያንቀሳቀስ የነበረውን የኬሚካል ጫኝ መርከብ በኢራን ሰው አልባ አውሮፕላን መመታቱንም ተናግረዋል፡፡

ለጋዛ ጦርነት መጀመር እና ለቀጣይነቱ አሜሪካን ተጠያቂ ያደረጉት ቃል አቀባዩ ፣ ዋሽኝግተን ለእስራኤል የምታደርገው እርምጃ እና ድጋፍ ከጊዜ ወደ ጊዜ በአለም አቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ ተቀባይነቷን እያሳጣት ነው ብለዋል።

አሜሪካ ኢራን ላይ ያቀረበችው መሰረተ ቢስ ውንጀላ በጋዛ እየተፈፀሙ ያሉ ወንጀሎችን ለመሸፈን ያለመ ፖለቲካዊ ጨዋታ ነው ያሉት ናስር ካናኒ ተቀባይነት እንደማይኖረውም ጠቁመዋል።

ኢራን በባህር ደህንነት ላይ በኃላፊነት ስሜት እየሰራች ነው እናም በዚህም በኩል በአለም አቀፍ ንግድ ውስጥ ትልቅ ሚና በመጫወት ላይ ትገኛለች ሲሉም ቃል አቀባዩ አመላክተዋል።

ከዚህም ጋር ተያይዞ አሜሪካ እና አጋሮቿ ኢራንን ለመክሰስ ምንም አይነት ሞራል ሊኖራቸው አይችልም በማለት እየቀረቡ ያሉ ትችቶችን አስተባብለዋል ሲል ፕረስ ቲቪ ዘግቧል።

በሀመረ ፍሬው
ታህሳስ 16 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply