ኢራን የ አሜሪካን የጦር መርከብ ከቀጠናዉ ለማባረር ቁርጠኛ መሆኗን አስታወቀች

የኢራን የባህር ኃይል አዛዥ አድሚራል ሻህራም ኢራኒ በፍልስጤም ያለውን ግጭት ምክንያት የተሰማራውን ትልቅ የአሜሪካ አዉሮፕላን ተሸካሚ መርከቦችን ከቀጠናዉ የውሃ ክልል ለማስወጣት ሀገራቸዉ ቆርጣ ተነስታለች ብለዋል።

የኢራን ባህር ሃይል በአካባቢው ከፍተኛ ተፅዕኖ ፈጣሪ ሃይል ሆኗል ያሉት ኢራኒ ኃይሉ በማንም ዉጫዊ ጫና አይገታም ብለዋል።

ድዋይት ዲ.አይዘንሃወር የተሰኘዉ የአሜሪካ የጦር መርከብ በቀጠናዉ ያለውን ወታደራዊ እና ፖለቲካዊ ሁኔታ ለመቀየር ወደ ክልሉ ገብቷል የሚለውን አባባል አዛዡ ዉድቅ አድርገዉታል።

ኢራኒ ጠላቶች በመካከለኛዉ ምስረቅ ክፍፍልን ለመዝራትና የራሳቸውን ፍላጎት ለማሟላት ቢገቡም በቅርቡ ከክልሉ እናስወጣቸዋለን ማለታቸዉን ፕሬስ ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡

አሜሪካ የጋዛዉ ጦርነት እንደተቀሰቀሰ ሁለት የጦር መርከቦችን ወደ አካባቢው መላኳ የሚታወስ ነዉ፡፡
ዋሽንግተን በወቅቱ የጦር መርከቦቹ የተላኩት ጦርነቱ ቀጣናዊ እንዳይሆን ለመከላከልና እስራኤልን ለመከላከል መሆኑን ስትገልፅ ነበር፡፡

ይሁን አንጅ ቴህራን የአሜሪካ የጦር መርከቦች ከቀጠናዉ አስወጣለሁ ስትል እየዛተች ነዉ

ቃልኪዳን በኩረፅዮን
ታህሳስ 02 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply