ኢሰመኮ በጂማ ዩኒቨርሲቲ ሁከት ፈጥራችኋል በሚል የታሰሩ ወጣቶች በፍርድ ቤት ነጻ ቢባሉም እስካሁን አለመፈታታቸውን አስታወቀ

ኢሰመኮ በጂማ ዩኒቨርሲቲ ሁከት ፈጥራችኋል በሚል የታሰሩ ወጣቶች በፍርድ ቤት ነጻ ቢባሉም እስካሁን አለመፈታታቸውን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 9 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በጂማ ዩኒቨርሲቲ ሁከት ፈጥራችኋል በሚል የታሰሩ ወጣቶች በፍርድ ቤት ነጻ ቢባሉም እስካሁን አለመፈታታቸውን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ከየካቲት 6 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ በእስር ላይ የሚገኘውን የወጣት ሙሃመድ ዴክሲሶንና በሱ መዝገብ የተከሰሱትን ሁለት ሰዎችን የፍርድ ቤት ሂደት በቅርበት እየተከታተልኩ ነው ብሏል።

ወጣቶቹ የታሰሩት በጂማ ዩኒቨርሲቲ ምርቃት ላይ ሁከት ፈጥራችኋል በሚል ተጠርጥረው ነው፡፡

የጂማ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት መጋቢት 7 ቀን 2013 ዓ.ም. ተከሳሾቹን በነጻ አሰናብቶ ከእስር እንዲለቀቁ ቢወስንም አሁንም በእስር ላይ ናቸው ሲል ኮሚሽኑ ገልጿል።

ስለሆነም  እስረኞቹ በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቁ በመጠየቅ የፍርድ ቤቶች ትዕዛዝ እንዲከበር አሳስቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

The post ኢሰመኮ በጂማ ዩኒቨርሲቲ ሁከት ፈጥራችኋል በሚል የታሰሩ ወጣቶች በፍርድ ቤት ነጻ ቢባሉም እስካሁን አለመፈታታቸውን አስታወቀ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply