
በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ወቅት የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን የሚመለከተው የሽግግር ወቅት የፍትህ አስተዳደር “እውነተኛ፣ ተአማኒ እና ግልጽነት ያለው” እንዲሆን ኢሰመኮ እንደሚያግዝ ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) ገለጹ። ኮሚሽነሩ እንደተናገሩት በሰላም ስምምነቱ ላይ የተጠቀሰው አይነት የሽግግር ፍትህ እንዲተገበር ኮሚሽኑ ከዚህ በፊት በምክረ ሀሳብ ደረጃ ማስቀመጡን አስታወሰው፣ ይህ እንዲሆን መወሰኑ “ትክክለኛ እርምጃ ነው” ብለዋል።
Source: Link to the Post