ኢትዮጵያችን እንዴት አደረች?! (ታህሳስ 22፣ 2013ዓ.ም) 1) የኢትዮጵያ  የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር” ኢትዮጵያ ከፍ ትበል” የሚል ገፅታ መገንቢያ ቃል በመምረጥ የኢትዮጵያን  ገፅታ ለማጉላት…

ኢትዮጵያችን እንዴት አደረች?! (ታህሳስ 22፣ 2013ዓ.ም) 1) የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር” ኢትዮጵያ ከፍ ትበል” የሚል ገፅታ መገንቢያ ቃል በመምረጥ የኢትዮጵያን ገፅታ ለማጉላት…

ኢትዮጵያችን እንዴት አደረች?! (ታህሳስ 22፣ 2013ዓ.ም) 1) የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር” ኢትዮጵያ ከፍ ትበል” የሚል ገፅታ መገንቢያ ቃል በመምረጥ የኢትዮጵያን ገፅታ ለማጉላት ዜጎቸ ተባበሩኝ ብሏል፡፡ በእርግጥ ተባበሩኝ ባይልኝ ሰው ለሀገሩ ቀናኢ ነበር፡፡ ነገር ግን በሀገራችን ያለው የሻገተ ፖለቲካ ኢትዮጵያን የሁላችን እንዳትሆን ስላደረገ በኢትዮጵዊነት ልቡ የሚሞቀው ሁሉ እየቀዘቀዘ ነው፡፡ ትግራይ በኤርትራ ተወርሬያለሁ ስትል ማጣራት አለመደረጉ፣ በጎንደር በኩል ሱዳን ስትወር አንዳንዱ ማጨብጨቡ፣ የደቡብ ሱዳን የሙርሌ ጎሳዎች ጋምቤላን የደም መሬት ሲያደርጓት፣ የሱዳን እና የሀገር ውስጥ ፅንፈኛ ሀይላት ተደራጅተው በመተከል እና በወለጋ ከ200ሺ በላይ ሲፈናቀል፣ በአምስት ወር ከአማራ ህዝብ ብቻ ከ2 ሺ ሰው በላይ ሲታረድ ሰሚ አ…ለመገኘቱ፣ የአንዱ ሞት የሌላው ድል ሆኖ መቀጠሉ ስለ ኢትዮጵያ በበጎ ላለመናገር አሳሪ ምክንያት ሆኗል፡፡ 2) የኢህአዴግ የነፍስ አባት የሆኑት አሜሪካዊዉ ኸርማን ኮኸን አብይ አህመድ የፖለቲካ ንግግር እና አካታች ስራዓት ካልገነባ ኢትዮጵያ የመውደቅ አደጋ ይገጥማታል ብለዋል፡፡ የ 2013 ምርጫም ደም አፋሳሽ ከመሆኑም ባሻገር በብልፅግና ብቻ የሚዘወር ይሆናል ብለዋል፡፡ አምሳደር ኸርማን ይሄን ያሉት በቲዊተር ገፃቸው ሲሆን፣ ከኦኤምኤን ጋርም በእንግድነት እንደሚቀርቡ ታውቋል፡፡ ኦኤምኤን ላይ ቀርበው ብልፅግናን እና ጠቅላላይ ሚኒስትር አብይ አህመድን መውቀሳቸው አይቀርም፡፡ 3) የትግራይ መከላከያ ሀይል ታጋይ ገብረ ገብረፃድቅ ” አለን፣ እየማረክን ነው ” አሉ፡፡ ታጋይ ገብረ አብይ አህመድ እና ብልፅግና እንታረቅ እያለ ሽማግሌ እየላኩብን ነው ብለዋል፡፡ ታጋይ ገብረ የት ሆነው መግለጫ እንደሰጡ አይታወቅም፡፡ መግለጫቸውም በድምፅ ሲሆን፣መግለጫ የሰጡት በድምፀወያኔ ዮቲብ በኩል ነው፡፡ ጌታቸው ረዳም ከሰሞኑ አለሁ አልሞትኩም ትግል ላይ ነኝ ያሉ ሲሆን ምናልባት ወደ ሱዳን ብዙዎቹ ሊወጡ ይችላሉ እየተባለ ነው፡፡ 4) በመተከል እና በቢሻንጉል መረጋጋት አልመጣም፡፡ በድባጤ ወረዳ የኦነግ ታጣቂዎች የገቡ ሲሆን ግጭቱ ወደ አሶሳም ሳይዛመት እንዳልቀረ እየተነገረ ነው፡፡ ኢ-መደበኛ ትጥቅ እና ስንቅ በብዛት እየተንቀሳቀ ሲሆን፣ የህወሓት አመራሮች ወደ ሱዳን ካመለጡ መተከልን የደም መሬት ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ መተከል የደም መሬት በሆነ ቁጥር የአባይ ግድብም የግብፅ የብቻ ፀጋ ይሆናል፡፡ 5) ብልፅግና ዓላማ ቢስ እና ምንም አይነት የወል ባህሪ ስለሌለው ዜጎችን የማዳን እድሉ ዝቅተኛ ነው፡፡ ብልፅግና ራሱን መሆን ተስኖት ያረጀ ኢህአዴግ ነው ያሉት ኢንጂነር ይልቃል ናቸው፡፡ ኢንጂነሩ ከአሻራ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቆይታ ብልፅግና የኢህአዴግ ብስባሽ ነው፡፡ ለዚህም በተመሳሳይ ሰው፣በተመሳሳይ ስራዓት፣ በተመሳሳይ ኢህአዴጋዊ ጥላቻ እየተመራ ነው ብለዋል፡፡ ብልፅግና የመንግስትነት ባህሪ የሌለው መሆኑ ደግሞ የበለጠ ከኢህአዴግ የባሰ አሸባሪ ድርጅት ሊያደርገው ይችላል ተብሏል፡፡ 6) በወለጋ የኦነግ ታጣቂዎች አንድ የኦሮሞ ባለሀብት የገደሉ ሲሆን፣ ባለሀብቱን የገደለው አማራ ነው በማለት በአማራ ላይ ጭፍጨፋ እንዲደረግ እየወተወቱ ነው፡፡ የጃልመሮ እናት ስለታሰሩ በኦነግ ደጋፊዎች ዘንድ ውስጣዊ ቁጣም ተቀስቅሷል፡፡ 7) በሰኔ 15 በባህርዳር ክስተት ጉዳይ አቶ ላቀ አያሌውን እና አቶ መላኩ አለበል ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች የምስክርነት ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን፣ ሁለቱ ከፍተኛ አመራሮች ብርጋዴር ጀኔራል አሳምነው ፅጌ ሲገድል አላየነም፡፡ ራሳችን በማዳን ውስጥ ስለነበርን ማን ምን እንዳደረገ ለመለየት አልቻልነም የሚል ይዘት ያለው ምስክርነት የሰጡ ሲሆን፣ በገዳይነት የተጠረጠሩት ብርጋዴር አሳምነው ፅጌ ሰኔ 17 ቀን ሲገደሉ፣ ሻምበል መማር ጌትነትም ተያዘ ተብሎ በማህበራዊ ሚዲያ የተነገረ ቢሆንም፣ እስካሁን አድራሻው እንዳልተገኘ ቤተሰቦቹ ሲናገሩ ተሰምቷል፡፡ 9) ባለስልጣናት ፖለቲካ አትፃፉ ተብለው በዶክተር ዓለሙ ስሜ ተግሳፅ ከደረሰባቸው በኃላ አብዛኛውን ባለስልጣናት ማህበራዊ ሚዲያ መጠቀም ሲያቆሙ፣ ቃለመጠይቅ ለመደረግም ወደ እነ አቶ ብናልፍ አንዷለም እና ዶክተር አለሙ ስሜ ማስፈቀድ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል፡፡ ያም ይህ ግን እነ ታየ ደንዳዓ ዛሬም እየፃፉ ይገኛሉ፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፈቃድ እንደሚፅፍም አሻራ በሹክሹክታ ሰምቷል፡፡ 10) ሁሉም የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ከዛሬ ጀምረው ከአረብ እና ከናይል ሳት ወርደው በኢትዮጵያ ሳተላይት መጠቀም ይጀምራል፡፡ አሻራ ለመላው ኢትዮጵያውያን መልካም ቀንን ይመኛል፡፡!!

Source: Link to the Post

Leave a Reply