ኢትዮጵያና ሶማሊያ ሁለተኛዉን ዙር ዉይይት ለማድረግ ተስማሙ

ኢትዮጵያና ሶማሊያ ሁለተኛ ዙር ውይይታቸውን ነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም በአንካራ ለመቀጠል እንደተስማሙ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአንካራው ውይይት ጉዳይ ባወጣዉ መግለጫ በቱርኪዬ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀካን ፊዳን ጋባዥነት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ እና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይና ዓለምአቀፍ ትብብር ሚኒስትር አህመድ ሞአሊም ፊቂ በአንካራ ተገናኝተው መወያየታቸውን አረጋግጧል።

የተካሄደው ውይይት በሁለቱ አገራት መካከል ላሉ አለመግባባቶች መፍትሄ ሊያመጡ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ግልፅና ወዳጅነት የተሞላበት የሀሳብ ልውውጥ የተደረገበት ነበር ብሏል።

ሁለቱ ሚኒስትሮች ያሉ አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ እልባት ለመስጠት ቁርጠኝነታቸውን መግለጻቸውን አስታዉቋል፡፡

ሁለቱ ሚኒስትሮች መልካም ጉርብትናን እና ቀጠናዊ መረጋጋትን ከግምት በማስገባት መፍትሄዎችን ለማመላከት ያለሙ ምክክሮችን ለመቀጠልም እንደተስማሙ አረጋግጧል።

ሚኒስቴሩ ሁለቱም ሚኒስትሮች የቱርኪዬ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ምክክሩን አገራቸው ለማስተናገድ የወሰዱትን ተነሳሽነት አድንቋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ሰኔ 25 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply