ኢትዮጵያን በኢትዮጵያውያን እናስተዋውቅ በሚል ለሁለት ወራት የሚቆይ የማህበራዊ ድረ ገፅ ዘመቻ ይፋ ሆነ

ኢትዮጵያን በኢትዮጵያውያን እናስተዋውቅ በሚል ለሁለት ወራት የሚቆይ የማህበራዊ ድረ ገፅ ዘመቻ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያን በኢትዮጵያውያን እናስተዋውቅ በሚል ለሁለት ወራት የሚቆይ የማህበራዊ ድረ ገፅ ዘመቻ ይፋ ሆኗል፡፡

የማህበራዊ ድረ ገፅ ዘመቻው ከታህሣሥ 21 ቀን 2013 እስከ የካቲት 14 ቀን 2013 ዓ.ም. ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ የቱሪዝም ሀብት፣ የተለያዩ ውሎችና የኢንቨስትመንት እድሎች ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ ዳያስፖራና ኤምባሲዎችን በማንቀሳቀስ በማህበራዊ ድረ ገፅ የሚካሄድ ነው ተብሏል።

በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ እንደተናገሩት ዘመቻው የቱሪዝም ሀብትን ይበልጥ በማስተዋወቅ ተደራሽነታቸውን በማስፋት የጎብኚዎችን ቁጥር በመጨመር ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው።

የሃገሪቱን ገፅታ የበለጠ ለመገንባትና ከኮቪድ 19 በኋላ በርካታ የውጭ ጎብኚዎችን ለመሳብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለውም ነው የተባለው፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

The post ኢትዮጵያን በኢትዮጵያውያን እናስተዋውቅ በሚል ለሁለት ወራት የሚቆይ የማህበራዊ ድረ ገፅ ዘመቻ ይፋ ሆነ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply