ኢትዮጵያን ወደ ሚፈለገው ደረጃ ለማድረስ የሙሉ ፕሮፌሰሮች ድርሻና ኃላፊነት ከፍተኛ ነው – ፕሮፌሰር አፈወርቅ

አዲስ አበባ፣ ጥር 14 ፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሮፌሰሮች ምክር ቤት 2ኛ መደበኛ ጉባኤ “ምሁራኖቻችን ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ግቦች” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ነው፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ በመክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያን ወደ ሚፈለገው ደረጃ ለማድረስ የኢትዮጵያውያን ሙሉ ፕሮፌሰሮች ድርሻና ኃላፊነት ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡

“ባለንበት ቦታና ደረጃ ላይ ሆነን ተሰናስለን ከሰራን ሀገሪቱን ወደምትፈልገው የእድገት ደረጃ እናደርሳለን˝ ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው እናንተ የኢትዮጵያ ልማትና ብልፅግና ግቦች ስኬት የጀርባ አጥንት ናችሁ” ሲሉ ገልፀዋል፡፡

ለሁለት ቀናት የሚካሄደው ጉባኤ ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ግቦች ስኬት ከፕሮፌሰሮች ምክር ቤት በሚጠበቁ ድጋፎች ላይ ይመክራል፡፡

ዝግጅቱ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ የችግኝ እንክብካቤ በማድረግ የተጀመረ ሲሆን  የዩኒቨርሲቲውን ላቦራቶሪዎች፣ ሰርቶ ማሳያዎችና የልህቀት ማዕከላትን ይጎበኛሉ ተብሏል።

በነገው ዕለትም በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የትኩረት መስኮች እና ከኢትዮጵያ ፕሮፌሰሮች ምክር ቤት በሚጠበቁ ድጋፎች ላይ ውይይት እንደሚካሄድ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ምክር ቤቱን ሲመሰርት ዋና ዓላማው ኢትዮጵያውያን ባለሙሉ ፕሮፌሰር ምሁራን ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በመቀናጀት የሳይንስ፣ ከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ግቦችን ለማሳካትና በሀገር ልማት አስተዋጽኦ የሚያደርጉበትን መንገድ ለመፍጠር ነው ተብሏል።ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

Source link

The post ኢትዮጵያን ወደ ሚፈለገው ደረጃ ለማድረስ የሙሉ ፕሮፌሰሮች ድርሻና ኃላፊነት ከፍተኛ ነው – ፕሮፌሰር አፈወርቅ appeared first on Satenaw Ethiopian News/Breaking News.

Source: Link to the Post

Leave a Reply