ኢትዮጵያን የሚያክል ታላቅ ሀገር ሉአላዊ የሆኑ ክልሎች የጋራ ጊዜያዊ መኖሪያ ቤት አድርጎ ያስቀመጠው ሕገ መንግስትና ጠንካራ መዋቅር አለመኖር በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚፈጠሩ ችግሮች ዋነኛ መንስኤ…

ኢትዮጵያን የሚያክል ታላቅ ሀገር ሉአላዊ የሆኑ ክልሎች የጋራ ጊዜያዊ መኖሪያ ቤት አድርጎ ያስቀመጠው ሕገ መንግስትና ጠንካራ መዋቅር አለመኖር በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚፈጠሩ ችግሮች ዋነኛ መንስኤ…

ኢትዮጵያን የሚያክል ታላቅ ሀገር ሉአላዊ የሆኑ ክልሎች የጋራ ጊዜያዊ መኖሪያ ቤት አድርጎ ያስቀመጠው ሕገ መንግስትና ጠንካራ መዋቅር አለመኖር በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚፈጠሩ ችግሮች ዋነኛ መንስኤ ናቸው ሲሉ የባልደራስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ገለታው ዘለቀ ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሞማ ታህሳስ 21 ቀን 2013 ዓ.ም… አዲስ አበባ ሸዋ “ኢትዮጵያ የገጠሟት ፈተናዎች እና የመሻገሪያ መንገዶችን” በተመለከተ ከአማራ ሚዲያ ማዕከል ጋር ቆይታ ያደረጉት የባልደራስ ቢሮ ሀላፊ አቶ ገለታው ዘለቀ ናቸው። ቀደምት አባቶቻችን በሀገር ምስረታው ረገድ በአለም አንደኛ እና ስኬታማ ነበሩ ያሉት አቶ ገለታው አሁን ላይ ያለው የእኛ ትውልድ የሀገር ግንባታውን የማስቀጠል ብዙ የቤት ስራ ተጥሎበታል ብለዋል። በውስጥ ያለውን ብዙሃነትን በማስተናገድ ረገድ ሲስተም በመፍጠር ከሚያለያዩን ይልቅ በሚያገናኙን ነገሮች ላይ ትኩረት በመስጠት ኢትዮጵያን ወደ አንድ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ማህበር ማምጣት ላይ የመስራት አስፈላጊነትን ጠቅሰዋል። አቶ ገለታው ሲቀጥሉ ኢትዮጵያን የሚያክል ታላቅ ሀገር ሉአላዊ የሆኑ ክልሎች የጋራ ጊዜያዊ መኖሪያ ቤት አድርጎ ያስቀመጠው ሕገ መንግስትና ጠንካራ መዋቅር አለመኖር በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚፈጠሩ ችግሮች ዋነኛ መንስኤ ነው ብለዋል። ክልሉን የ5 ነባር ብሎ የጠራቸው ብሄረሰቦች አድርጎ ያስቀመጠና ቀሪዎችን ሌሎች ብሎ የሰየመው ከፋፋይ የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ህገ መንግስትንና በሌላ በኩል አንድ ዜጋ የትም ተንቀሳቅሶ የመኖርና የማልማት መብት አለው በሚለው የኢትዮጵያ ህገ መንግስት ላይ ያለውን ተቃርኖ እንደ ምሳሌ ጠቅሰዋል። በተጨማሪም የአማራ ክልል ህገ መንግስት በክልሉ ውስጥ ላሉ ዜጎችን እኩል እንደ አንድ በማየት እውቅና የሚሰጥ ቢሆንም እንደኦሮሚያ፣ቤንሻንጉልና የመሳሰሉት ክልሎች ህገ መንግስት እውቅና አይሰጥም ብለዋል። ኢትዮጵያ ግልፅ የሆነ የመተሳሰሪያ መርሆ የሌላት ሀገር ሆናለች ያሉት አቶ ገለታው አንዳንድ አሉ የሚባሉ መተሳሰሪያዎች ቢኖሩም እነሱን የሚሰባብሩ ህጎች በየክልሎች ይታያሉ ብለዋል። “በመዋቅር ደረጃ በአጠቃላይ ኢትዮጵያ አላት የምንለው ህገ መንግስት አይመጥናትም፤ ኢትዮጵያን ያክል ሀገር እንደፈለገ ልትፈርሽ ትችያለሽ ብሎ የሚደነፋባት ህገ መንግስት አይመጥናትም” ሲሉ ተናግረዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply