ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለም የተለያዩ ሀገራት የእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን በድምቀት አክብረዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 30 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ…

ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለም የተለያዩ ሀገራት የእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን በድምቀት አክብረዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 30 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ኢትዮጵያን ጨምሮ በዓለም የተለያዩ ሀገራት ተከብሮ ስለመዋሉ የቢቢሲ ዘገባ አመልክቷል። በኢትዮጵያ የገና በዓል በተለያዩ አካባቢዎች መከበሩ እንዳለ ሆኖ በድምቀት ከሚከናወንባቸው አካባቢዎች አንዱ በሆነው በተለይም በላሊበላ በቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን በገና ዋዜማ እና በዕለቱ በካህናት የተመራ ደማቅ ኃይማኖታዊ ሥርዓት ተካሂዷል፡፡ ኢትዮጵያን ጨምሮ ኤርትራ፤ ግብፅ፣ ሩሲያ፤ ዩክሬን፤ ቤላሩስ፤ ካዛኪስታን፤ ሰርቢያ፤ ሞንቴኔግሮ፤ እስራኤል፤ ቡልጋሪያ፤ መቄዶኒያ፤ ጆርጂያና ሞልዶቫ ዛሬ የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ተከብሯል። አውሮፓ እና አሜሪካንን ጨምሮ በርካታ የዓለም አገራት ክርስቲያኖች የገና ወይም የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን የሚያከብሩት ከዘመን መለወጫቸው አንድ ሳምንት ቀደም ብሎ ታኅሣሥ አጋማሽ ላይ ነው። እነዚህን አገራት የሚያመሳስላቸው አንድ ጉዳይ በርካታ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት እምነት ተከታይ ስላላቸው ሲሆን፣ ሌላኛው ደግሞ የሚከተሉት የዘመን አቆጣጠር ነው። ልክ እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ የኮፕቲክ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ገናን ከምዕራቡ ዓለም በሁለት ሳምንታት ያህል ዘግይተው ያከብራሉ። የጥምቀት እና የፋሲካ በዓልን የሚያከብሩበት ቀንም ከምዕራቡ ዓለም ጋር በተመሳሳይ ልዩነት ያለው ስለመሆኑ ተገልጧል። በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች አብዛኞቹ የጁሊያን አቆጣጠርን በመከተል የገናን በዓል የሚያከብሩት በፈረንጆቹ ጥር 7 ቀን ነው። ሁለቱ ብዛት ያለው የእምነቱ ተከታይ ያላቸው ሀገራት፣ ሩሲያ እና ዩክሬን ፤ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ በአውሮፓ ትልቁ የተባለውን ጦርነት እንደቀጠሉ ቢሆንም በዓለም ዙሪያ ያሉ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች በዛሬው ዕለት ገናን ስለማክበራቸው የቢቢሲ ዘገባ አመላክቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply