ኢትዮጵያዊቷ ስደተኛ በፖላንድ ድንበር ሴት ልጅ ተገላገለች፡፡

የፖላንድ የድንበር ጠባቂ ወታደሮች ኢትዮጵያዊቷን ስደተኛ በሰላም እንድትገላገል ያበረከቱት አስተዋጽኦም ከፍተኛ መሆኑን ተዘግቧል፡፡

ፖላንድ ከቤላሩስ ጋር በምትዋሰንበት ድንበር አቅራቢያ የነበረችን በህገወጥ መንገድ ፖላንድ ለምግባት የሞከረችውን ኢትዮጵያዊት ስደተኛ በተደረገላት እገዛ ሴት ልጅ ተገላግላለች፡፡

በህገወጥ ስደት ወደ አውሮፓዊቷ ሀገር ፖላንድ ለመግባት በጉዞ ላይ የነበረችው ይህች ኢትዮጵያዊት ለበርካታ ሰአታት ካማጠች በኃላ የፖላንድ የድንበር ጠባቂዎች ባደረጉላት እገዛ ነው በሰላም ልትገላገል የቻለችው ተብሏል፡፡

የፖላንድ የድንብር ጠባቂዎች ወጣቷ ኢትዮጵያዊት በምጥ ላይ መሆኗን በመረዳት ወደ ቦታው አፋጣኝ አምቡላንስ እንዲመጣ ቢያደርጉም አምቡላንሱ ከመምጣቱ አስቀድሞ ወጣቷ በሰላም መገላገሏን ወታደሮቹ ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ እናትና ልጅ በተደረገላቸው ድጋፍ በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ የገለጹት የፖላንድ መገናኛ ብዙሃን እስኪያገግሙ ድረስ በሆስፒታል ይቆያሉ ብለዋል፡፡

በድርጊቱ የፖላንድ ወታደሮች ያደረጉት በጎ ተግባር የሃገሪቱ የጤና ሚኒስትር ምስጋናቸውን ችረዋቸዋል ሲል tvn24 ዘግቧል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ሰኔ 11ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply