
ከአራት ዓመታት በፊት በገጠማት ጉዳት ምክንያት በሐኪሞች ሩጫ እንድታቆም የተመከረችው ትዕግሥት፣ ባለፈው ሳምንት መስከረም 13/2016 ዓ.ም. ጀርመን ላይ ከባዱን የማራቶን ውድድር ክብረ ወሰን በሰፊ የሰዓት ልዩነት በማሻሻል ዓለምን አስደንቃለች። ይህንን የሴቶች ማራቶን ክብረ ወሰንን በሁለት ደቂቃ ከ11 ሰከንዶች ለማሻሻል ዓመታትን እና ከፍተኛ ልፋትን እንደሚጠይቅ በስፖርት ተንታኞች እየተነገረ ነው።
Source: Link to the Post