ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ዘርፌ ወንድማገኝ ለአምስት ዓመታት ከአትሌቲክስ ታገደች:: የ21 ዓመቷ የመካከለኛ ርቀት አትሌት ለአምስት ዓመታት መታገዷን የገለጠው አትሌቲክስ ኢንቴግሪቲ ዩኒት የተባለው…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/dVza1z91qDS3OVZy9oN2JDMn0Gz68uVFV5ZM-dnLQoy_bZXgtn2pO1qsOrNNjF-Uk2irTwJ_WK7ZImQSV-QmY8D-XXGdlm4VJ4k9nfstVdbPy-xhvGY9CRWaG9RyrnpSTyzBZtW6FwcELsun6GTGIuPcENevEv1_7Mkyl51CPB3o59hIjtmZKin90y1zj9VgKh9I8AFu2qvwRyDk7NBonhqZDdTwtT_MoKqU8vW8xlRc7dg27U3frY9w1BJqrj6S588xFugChGkBbmxXW3k1Am21_xNHsM33E5zIWL_TM6QTHI9JHNRFSl_eHozSVoZ329_vnrw9De75MiAf2nA9Uw.jpg

ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ዘርፌ ወንድማገኝ ለአምስት ዓመታት ከአትሌቲክስ ታገደች::

የ21 ዓመቷ የመካከለኛ ርቀት አትሌት ለአምስት ዓመታት መታገዷን የገለጠው አትሌቲክስ ኢንቴግሪቲ ዩኒት የተባለው ተቋም ነው።

ተቋሙ በቀድሞው ትዊተር በአሁኑ ኤክስ ሰሌዳው ላይ በለጠፈው መግለጫ አትሌቷ ምርመራ ከተደረገላት በኋላ ቅጣት ማስተላለፉን አሳውቋል።

የዓለም አትሌቲክስ አካል የሆነው ይህ ተቋም ባወጣው መግለጫ፣ አትሌቷ ሁለት የተከለከሉ ንጥረ-ነገሮችን መውሰዷን አምናለች ብሏል።

ዘርፌ፤ ቴስቶስቴሮን የተባለውን እና ኢፒኦ የተሰኘውን አትሌቶች በደማቸው ውስጥ የበለጠ ኦክሲጅን እንዲኖር የሚያደርግ ንጥረ ነገር መውሰዷን አምናለች።

ዘርፌ በቶኪዮ ኦሊምፒክስ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ስምንተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋ ይታወሳል።

በጋዲሳ መገርሳ

ሚያዝያ 14 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply