ከሁለቱም ተቋማት ስያሜ በመዋስ ዳን ኢንዱስትሪ ፋይቭ የተባለ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ማመርቻ በዳን ኢነርጂ ስማርት ህንፃ ላይ ለማምረት በዛሬው ዕለት የስምምነት ፊርማ ተፈራርመዋል፡፡
5.0 የተባለው አዲስ የቴክኖሎጂ ውጤት በመጠቀም የተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በተለይም ላፕቶፕ እና ታብሌቶችን ማምረት እንደሚጀምሩ የዳን ኢነርጂ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዳንኤል ሀይሉ ተናግረዋል፡፡
ምርቶችን እዚሁ ሀገር ውስጥ በመገጣጠም በተመጣጣኝ ዋጋ በሀገር ውስጥ እንዲሁም ለአፍሪካ ገበያ እንደሚያቀርቡም አስታውቀዋል፡፡
የቴክኖሎጂ ሽግግር ስልጠናው እንደተጀመረ የገለፁት አቶ ዳንኤል በቅርቡም ሙሉ በሙሉ ወደ ምርት እንደሚገቡ ተናግረዋል፡፡
የተወሰኑት ግብዓቶች እዚሁ የሚመረቱ ሲሆን የተወሰነው ደግሞ ዓለም ላይ ተዋቂ ከሆኑ የቴክኖሎጂ ድርጅቶች ኢንቴል እና ማይክሮሶፍትን ከመሳሰሉት ግብዓቶች በማስመጣት የሚገጣጠም ይሆናል።
የመገጣጠም ስራውም ከዩኒቨርሲቲ ተመርቀው በዳን ኢነርጂ ስልጠና በሚሰጣቸው ወጣቶች ይከናወናል ተብሏል፡፡
ዳን ኢነርጂ 5.0 ቴክኖሎጂን የሚጠቀም ስማርት ህንፃ የገነባ በመሆኑ አንድ አንድ አድካሚ ስራዎችን ሮቦቶችን በመጠቀም እንደሚሰራ ተገልፃጿል፡፡
በዳን ኢንዱስትሪ ፋይቭ ሁለት የተለያዩ ብራዶች የሚመረቱ ሲሆን አትላስ እና ሲል የሚባሉ፦ መሆናቸውን አቶ ዳንኤል ገልፀዋል፡፡
በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥም አንድ ሚሊዮን የሚሆኑ ላፕቶፖች፣ስልኮች እና ታብሌቶችን ለማምረት መታቀዱንም አቶ ዳንኤል ነግረውናል፡፡
ለ300ሺ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን የሰራ ዕድል እንደሚፈጥርም ጨምረው ገልጸዋል።
በአቤል ደጀኔ
ሐምሌ 07 ቀን 2015 ዓ.ም
Source: Link to the Post