
ግዙፉ የማኅበራዊ ሚዲያ መድረክ ፌስቡክ ከተለያዩ ወገኖች ቅሬታ እና ክስ ሲቀርብበት ቆይቷል። በፌስቡክ ላይ የሚሰራጩት መልዕክቶች ጥላቻ እና ግጭቶችን በማባባስ በተደጋጋሚ እየተወቀሰ ነው። ከዚህ ባሻገርም በፌስቡክ በኩል የሚቀርቡ ጎጂ ይዘቶችን መቆጣጠር የሆኑ ሠራተኞችም በየዕለቱ በሚመለከቷቸው አሰቃቂ ነገሮች ምክንያት ለጤና ቀውስ ተጋልጠናል በሚል ብሶታቸውን እያሰሙ ነው። ከእነዚህም መካከል ኢትዮጵያውያንም ይገኙበታል።
Source: Link to the Post