ኢትዮጵያውያኑን አማራን አድኖ መግደል ይቁም!!! ቢንያም ሙሉጌታ ከኖርዌ

በሀገራችን ኢትዮጵያ በአራቱም አቅጣጫ ህወሃት ወያኔን እየናጠ የሚገኘው ተቃውሞ አምባ ገነኖቹ የህወሃት ወያኔ
ባለስልጣናትን የስልጣን ዘመናቸው ማብቂያ ደውል መሆኑን አረጋግጦላቸዋል።
በውድቀት አፋፍ ላይ የሚገኘው ህወሃት ወያኔ በሁሉም አቅጣጫ የኢትዮጵያ ክፍል ላይ የተነሳበትን ተቃውሞዎች
መልካቸውን ቀይረው ወደ እርስ በርስ ግጭት እንዲያመራ ለማድረግ ሲሞክር በከፊልም ሲሳካለት እየተመለከትን
ነው ህወሃት ወያኔ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል የሚለው አቋሙ በግልጽ ታይቷል።
ለዚህም እንደማሳያ ሁለት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በኦሮምያና ሶማሊያ ክልል በወያኔ ህወሃት መሪነት የተነሱት
የእርስ በርስ ግጭቶች ማስታወስ ያስፈልጋል። ዜጎች ከገዛ ሀገራቸው ሲፈናቀሉ ከመቶ ሺ በላይ የሚሆኑ ኦሮሞዎች
ከሱማሊያ ክልል ሀብት ንብረታቸው ተዘርፈው ሲሰደዱ ሴቶቻቸው በሱማሊያ ሚሊሻ ሲደፈሩ ሲገደሉ አይተናል።
ታዲያ ይህ ሁሉ አምባገነኑ ህወሃት ስልጣኑን ለማራዘም የሚጠቀምበት እንደሆነ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የተደበቀ
አይደለም። ህወሃት ወያኔ ኢትዮጵያን ለማተራመስ ቀርፆ በሚጠቀመው ፖሊሲ መሠረት በሁሉም የኢትዮጵያ
ክልሎች ላይ የዜጎችን ዘርን ተገን ያደረገ የእርስ በርስ ግጭት እያነሳሳ ይገኛል።
ባሳለፍናቸው ሁለት ቀናቶች ውስጥ እንኳን በኢሊባቡር ከ 20 በላይ አማሮች በግማሽ ቀን ውስጥ ተጨፍጭፈዋል
ተገለዋል በኢሊባቡር ወረዳዎች የአማራ ተወላጅ የሆነ ተለይተው እየተጠቁ እንደሆነ የተጎጂ ቤተሰቦች ሲናገሩ
አድምጠናል። ስርዓቱን በመቃወም የተጀመረው የተቃውሞ ሰልፍ በህወሃት ወያኔዎች ሰርጎ ገብነት ሆን ተብሎ
አላማውን እንዲስት ተደርጉዋል።
በኢሊባቡር ደጋ የተፈናቀሉ አማራ ሴቶች በተሰደዱበት ጫካ ውስጥ እንዳሉ ሁለት ነፍሰጡሮች መውለዳቸው ተነግሯል።
በጅማ ዞን ሊዪ ወረዳ የአማራ ተወላጆች ንብረት እየወደመ እንደሆነ አድምጠናል ብዙ ወራትን ያስቆጠረው የአማራ
ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ጥቃትም የአማራ ልጆች ከትምህርት ገበታ ጭምር አስተጓጉሎ እንዲታገዱ አድርጉዋል።
ሀላፊነቱን መውሰድ ያለባቸው የዚህ ሁሉ ሴራና ተንኮል አቀናባሪዎች የህወሃት ወያኔ ቱባ ባለስልጣናት ናቸው።
ሴራቸውና ተንኮላቸው ተግባራዊ እንዲሆን ትዕዛዝ የሰጡት እነዚሁ ህወሃቶች የሚፈልጉት ደም መፋሰስና ግጭት ብቻ
ነው።
ስለዚህ አማራው ሆነ ሌላው ኢትዮጵያዊ በንፁሃን ወገኑ ላይ የደረሰውን ጅምላ ጭፍጨፋ አፀፋውን በመመለስ
መቃወም ይገባዋል። ህወሃት ወያኔ ሲገድለን ሲያስገድለን 26 ዓመታት አስቆጥሯል ለገደለን ላስገደለን ጠላታችን
ህወሃት ርህራሄ ፍፁም አያስፈልግም። በህወሃት ወያኔ ምክን ያት ከዚህ በኃላ ደሀው ኢትዮጵያዊ ወገናችን ተቸግሮ
ተሰቃይቶ መኖር ሊበቃው ይገባል።
ወያኔ የውድቀት ጫፍ ላይ ያደረሰው የገዛ ማንነቱና ባህሪው ነው የአንድ ዘር የበላይነትን አንግሶ ሌላውን ኢትዮጵያዊ
ዜጋ እንደ መጤ ወይም እንደ ሁለተኛ ዜጋ በበታችነት ዐይን እያየ የአንድ አካባቢ ሰዎችን ተጠቃሚ ያደረገ ሲስተም
ዘርግቶ ሌላውን ያገለለችና ተጠቃሚ ያላደረገች ኢትዮጵያ ለመፍጠር ሲሞክር ከመላው ኢትዮጵያዊ የመረረ
ተቃውሞዎች አንገዛም ህወሃት ወያኔ በቃን የሚል መልእክት እየተስተጋባ ነው ያለው።
ብዙ ተምሮ ስራ ያጣ ወጣት ሀገሪቱን ሞልቷል የውትድርና ልምድ ባላቸው የወያኔ ባለስልጣናት የምትመራው ሀገር
ኢትዮጵያ ዛሬም አድጋለች እያሉ ህዝቡን ሊያደነቁሩት ሲሞክሩ ታዝበናል። ውስን የወያኔ አገልጋዮችና ባለስልጣናት

የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ተቆጣጥረው ቀሪውን የሀገሪቱን ዜጋ በርሀብ ጠብሰውት የበይ ተመልካች ሆኖ ባለበት በዚህ ሰዓት
ይህ የተራበ ሕዝብ መሪውን ሊበላ ደርሷል።አሁን በሀገራችን ያለው ነውጥ ወደ ለውጥ ለመቀየር ሁሉም ዜጋ
በአንድነት ተነስቷል። ህወሃት ወያኔ ለመውደቅ መንገዳገድ ጀምሯል የተንገዳገደውን አምባ ገነኑን ስርዓት የመጣል
ሀላፊነት የህዝቡ ነው የለውጡም ባለቤት የሚሆነው ህዝቡ ነው።
የወያኔ ህወሃት ድርጅት አባላት በተናጠል ከወያኔ ጋር በማበር ህዝቡን የምታስጨፈጭፉት የኢትዮጵያ ህዝብ ሲደማ
ምሽቱን ዳንኪራ የምትመቱ በገንዘብና በሌላም በሁሉ አቅጣጫ ከጎናቸው ያላችሁ ከአንድ አካባቢ የተሰበሰባችሁ
እየሰራችሁ ያለው ታሪክ ተመዝግቦ የሚቀመጥ በደል ግፍ ትልቅ ዋጋ የሚያስከፍላችሁ መሆኑን እወቁት።
አሁን የተጀመረው ህዝባዊ እንቅስቃሴ አድማሱን በማስፋፋት ትግሉን ወደ መጨረሻ ደረጃ ላይ መግፋቱ ልብ ልንል
ይገባል የመጨረሻውን ውጤት ማሳመር እንዲቻል ትግሉን መደገፍ አለብን።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

Leave a Reply