You are currently viewing ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ያሉበት የጅምላ መቃብር በማላዊ መገኘቱ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ጥቅምት 10 ቀን 2015 ዓ.ም         አዲስ አበባ ሸዋ በማላዊ 25 ኢትዮጵያውያን…

ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ያሉበት የጅምላ መቃብር በማላዊ መገኘቱ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 10 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በማላዊ 25 ኢትዮጵያውያን…

ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ያሉበት የጅምላ መቃብር በማላዊ መገኘቱ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 10 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በማላዊ 25 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ያሉበት የጅምላ መቃብር መገኘቱ ተገልጧል። ምዚምባ በሚባለው የማላዊ ሰሜናዊ ግዛት በሚገኝ ጥብቅ ደን ውስጥ በተገኘው የጅምላ መቃብር የኢትዮጵያውያን ስደተኞች አስክሬን መገኘቱን የአገሪቱ ፖሊስ አረጋግጧል። በጥብቅ ደኑ በተገኘ የጅምላ መቃብር ውስጥ የተገኙት 25 የስደተኞች አስክሬኖች የኢትዮጵያውያን እንደሆኑ ፖሊስ ገልጿል። “በስፍራው የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ተጎጂዎቹ ኢትዮጵያውያን ናቸው” ሲል የማላዊ ፖሊስ ባወጣው መግለጫ አብራርቷል። ሁሉም ዕድሜያቸው ከ25 እስከ 40 እንደሆነና በምን ምክንያት እንደሞቱ ምርመራ እየተካሄደ እንደሚገኝ ተገልጿል። ከዓመቱ መባቻ ጀምሮ 221 ስደተኞች እንደተያዙና ከእነዚህ መካከል 186ቱ ኢትዮጵያውያን እንደሆኑ ፖሊስ ተናግሯል። ማላዊ ውስጥ የሚያዙ አብዛኞቹ ስደተኞች በማላዊ በኩል ወደ ደቡብ አፍሪካ፣ አውሮፓ እና አሜሪካ የሚሻገሩ መሆናቸው በተደጋጋሚ ይገለጻል። ከዚህ ቀደምም የስደተኞች አስክሬን በማላዊ እና ሞዛምቢክ ተገኝቷል። ያለፈው ሰኔ የመንግሥታቱ ድርጅት ባወጣው መግለጫ በማላዊ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ውስጥ በርካታ የሕገ ወጥ ሰዎች ዝውውር ሰለባ የሆኑ ኢትዮጵያውያን እንደሚገኙና ብዝበዛ እንደሚደርስባቸውም ማስታወቁ አይዘነጋም። ድዛሌካ በተሰኘው የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ውስጥ በወንዶች፣ በሴቶች እና በሕጻናት ላይ መጠነ ሰፊ ብዝበዛ እንደሚደርስ ይፋ የተደረገው በተባበሩት መንግሥታት የመድኃኒት እና የወንጀል ጽሕፈት ቤት (ዩኤንኦዲሲ) እና የማላዊ ፖሊስ ባደረጉት የጥምረት ክትትል ነው። ተቋሙ ከ90 በላይ ሰለባዎችን መታደጉን ገልጾ፣ አብዛኛዎቹ ከ18 እስከ 30 ዓመት የሚሆናቸው ኢትዮጵያውያን ወንዶች ናቸው ብሏል። ሌሎቹ ደግሞ ከ12 እስከ 24 ዕድሜ ያሉ ታዳጊዎችና ሴቶች ሲሆኑ የኢትዮጵያ፣ የብሩንዲ እና የዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ዜጎች ናቸው። በስፍራው ገበያ በሚመስል ሁኔታ ታዳጊ ልጆች የሚሸጡበትና እነዚህም ለግዳጅ ሥራ እና ለወሲብ ንግድ ብዝበዛ እንደሚዳረጉ የዩኤንኦዶሲ ተወካይ ማክስዌል ማትዌር ተናግረዋል። ዩኤንኦዲሲ ሰኔ ላይ ያወጣው ሪፖርት፤ የሕገ ወጥ ሰዎች ዝውውር ሰለባ ከሆኑት መካከል የአሥር አመት ታዳጊ ትገኝበታለች ብሏል። አንዳንድ ስደተኞች እንደተደፈሩ፣ ድብደባ እንደደረሰባቸው እንዲሁም ሕጻናት ለአስገዳጅ የግብርና ሥራ እንደተዳረጉ ሪፖርቱ ጠቅሷል። ከእነዚህም ውስጥ የተወሰኑ ታዳጊ ሴቶች በሕገ ወጥ ዝውውር በደቡብ አፍሪካና በሌሎች አገራት ለወሲብ ንግድ የሚሸጡ ሲሆን፤ በርካቶችም ብዝበዛ እንደረሰባቸው ሪፖርቱ አጋልጧል። ወንድ ስደተኞችም በመጠለያ ካምፑ ውስጥ ባሉ እርሻዎች እንዲሁም በማላዊና በሌሎች አገራት በግዳጅ እየሠሩ እንደሆነ በመጥቀስ ሁኔታው አሳሳቢ ነው ብሏል። የመጠለያ ካምፑ በሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ማዕከልነት እያገለገለ መሆኑንና ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ሰለባዎችን በሐሰተኛ ሽፋን በመመልመል ድንበር አቋርጠው ወደ ማላዊ ያመጧቸዋል ብሏል። ሰለባዎቹም ደቡብ አፍሪካ ለሥራ ትወሰዳላችሁ በሚል ማታለያ ከኢትዮጵያ፣ ብሩንዲና ኮንጎ የተወሰዱ ሲሆን በካምፑ ውስጥ እስከ ማላዊ ድረስ የተወሰዱበትን ብር እንዲከፍሉ እንደሚገደዱም ሪፖርቱ አትቷል። በመጠለያ ካምፑ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የሕገ ወጥ ሰዎች ዝውውር ሰንሰለቶችን ለመቆጣጠር፣ ሰለባዎችን ለመለየት እንዲሁም ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን ለፍርድ ለማቅረብ እርምጃዎችን በመወሰድ ላይ መሆኑም ተገልጿል። ሪፖርቱ በወጣበት ወቅት ከሦስቱም አገራት አምስት ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች በቁጥጥር ሥር እንደዋሉ ቢገለጽም፤ በርካታ ተጎጂዎች ምስክርነት ለመስጠት በመፍራታቸው ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ወስዶ ፍትሕ ለማግኘት እክል መግጠሙ ተመልክቷል። እአአ በ1994 የተቋቋመው የድዛሌካ የስደተኞች ካምፕ በማላዊ ትልቁ ሲሆን 50 ሺህ ስደተኛና ጥገኝነት ጠያቂዎችን ይዟል። ቢቢሲ አማርኛ እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply