ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በህንድ ዴልሂ የግማሽ ማራቶን ውድድር አሸነፉ

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በህንድ ዴልሂ የግማሽ ማራቶን ውድድር አሸነፉ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአለም የግማሽ ማራቶን የነሀስ ሜዳሊያ ተሸለሚዋ ያለምዘርፍ የኋላው የህንድ ዴልሂ ግማሽ ማራቶንን የቦታውን ሰአት በማሻሻል አሸነፈች።
ኢትዮጵያዊቷ አትሌት የአለም ምዘርፍ የኃለው በ64:46 1ኛ በመውጣት ስታሸንፍ፣ አባበል የሻነው በ65:21 3ኛ፣ ፀሀይ ገመቹ በ67:16 5ኛ በመውጣት ውድድሩን አጠናቀዋል።
በሩጫው ኬንያውያን አትሌቶች 2ኛ እና 4ኛ ወጥተዋል።
በተመሳሳይ በወንዶች አትሌት አምደወርቅ ዋለልኝ በ58:53 የቦታውን ሰአት ሲያሻሽል፣ አንዱአምላክ በልሁ በ58:54 2ኛ፣ ሙክታር በ59:04 4ኛ እና ተስፋሁን አካልነው በ59:22 6ኛ በመውጣት ውድድሩን ፈፅመዋል።

The post ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በህንድ ዴልሂ የግማሽ ማራቶን ውድድር አሸነፉ appeared first on Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C.

Source: Link to the Post

Leave a Reply