
“በልጅነቴ ብዙ ጫማ አልነበረኝም። ዓመቱን ሙሉ የሚገዛልኝ አንድ ብቻ ነበረ። ከፕላስቲክ የሚሰራው ጫማ ሲያረጅ ብረት በማጋል መጠገን የተለመደ ነገር ስለነበረ አንዱ ጫማ ቢያንስ ለግማሽ ሴሚስተር ያቆየኝ ነበር። እኔ ቢያንስ አንድ ጥንድ ጫማ ነበረኝ፤ ብዙ ጓደኞቼ ግን ጫማ የሚባል አልነበራቸውም” ስትል በጨቅላ ዕድሜዋ ያስተዋለችውን ታስታውሳለች።ታድያ ይህ የልጅነት ሕይወቷ መነሻ ሆኗት ለሌሎች ታዳጊዎች ጫማ የሚደግፍ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት አቋቁማለች፤ መዓረግ።
Source: Link to the Post