ኢትዮጵያ፣ሱዳንና ግብፅ በሰሞነኛው የኅዳሴ ግድብ ድርድር ስምምነት ላይ አለመድረሳቸውን አስታወቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ጥቅምት 26 ቀን 2013 ዓ.ም           አዲስ አበባ ሸዋ…

ኢትዮጵያ፣ሱዳንና ግብፅ በሰሞነኛው የኅዳሴ ግድብ ድርድር ስምምነት ላይ አለመድረሳቸውን አስታወቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 26 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ…

ኢትዮጵያ፣ሱዳንና ግብፅ በሰሞነኛው የኅዳሴ ግድብ ድርድር ስምምነት ላይ አለመድረሳቸውን አስታወቁ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥቅምት 26 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የሦስቱ አገራት የውሃ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጥቅምት 25 በበይነ መረብ ድርድር ቢያደርጉም ባነሷቸው ጉዳዮች ላይ መስማማት አልቻሉም። ቀደም ባሉት 2 ቀናት በአገራቱ ባለሙያዎች የተደረገው የሦስትዮሽ ድርድር ሪፖርትም ለሚኒስትሮቹ ድርድር መድረክ ቀርቧል። ሚኒስትሮቹ በቀጣዩ ድርድር አካሄድ፣ የአፍሪካ ኅብረት ባለሙያዎች ሚና እንዲሁም የጊዜ ሰሌዳ ላይ ትኩረት አድርገው መምከራቸውን ያሳወቀው የኢትዮጵያ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር ውይይት በተደረገባቸው ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ሙሉ ስምምነት መድረስ አለማቻሉን አሳውቋል። ኢትዮጵያ አገራቱን የሚያቀራርብ አማራጭ ማቅረቧንም ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ አክሏል። በድርድሩ ቀጣይ አካሄድ ዙሪያ ለመምከር ለአፍሪካ ኅብረት የአስፈፃሚዎች ምክር ቤት ሊቀመንበር እና ለደቡብ አፍሪካ ዓለም ዐቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስቴር ሦስቱም አገራት የተናጠል ሪፖርት ለማቅረብ ተስማምተው ስለመለያየታቸው የዘገበው አሐዱ ቴሌቪዥን ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply