ኢትዮጵያ፣ ሱዳን ከጠብ አጫሪ ድርጊቷ እንድትቆጠብ አሳሰበች፡፡የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣዉ መግለጫ የሱዳን መከላከያ በድንበር አካባቢ ያለዉን ዉጥረት ምክንያት በማድረግ እያደረገ ካለዉ ት…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/IBC382Sm1KrYnjFDM7YFsPX0WaFzLeA-xjwY1K13mUf-NhhPxbS6JHWweZOE1z1-A1cUT_ABN5txKDNAFmPXGHIcOMySOy-LDu4aE12quPcHPJTKwe768sGFZCtVwKBin8Gqbg5_uDeFkxVS7Rcco0u8n25NYyqfqTa0DxT-Y9JXi1fH2r9Qkdc81BdZBVdQ7iKKjIYspLM9fQT7lBK3-erWnPmNPkUrVP_njo96AppxTinL2UCuOPRUKB27rmebm_uTTyKvtbPcGg0YUVktWPtrxMv_k4pUCg0fVcMlYWrBYXQNdoOzEJMZm3awChpC8wi4ZqsiJAUJ3CyEPu95_w.jpg

ኢትዮጵያ፣ ሱዳን ከጠብ አጫሪ ድርጊቷ እንድትቆጠብ አሳሰበች፡፡

የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣዉ መግለጫ የሱዳን መከላከያ በድንበር አካባቢ ያለዉን ዉጥረት ምክንያት በማድረግ እያደረገ ካለዉ ትንኮሳ እንዲቆጠብ አስጠንቅቋል፡፡
የሱዳን ወታደሮች ከህወሓት ሃይሎች ጋር በመሆን የኢትዮጵያን ድንበር አልፈዉ ጥቃት መፈጸማቸዉን የገለጸዉ መግለጫዉ ጉዳዩን አጣርቶ ይፋ እንደሚያደርግ አስታዉቋል፡፡

ግጭቱን ያስነሱት የሱዳን ወታደሮች ሆኖ ሳለ የሀገሪቱ መከላከያ መስሪያ ቤት ኢትዮጵያን መዉቀሱ ተገቢ እንዳልሆነም አንስቷል፡፡
ግጭቱን የፈጠሩ አካላት የሁለቱን ህዝቦች ግንኙነት ለማበላሸት ነዉ ብሎ የኢትዮጵያ መንግስት እንደሚምን ገልጧል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለዉን አለመግባባት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ዝግጁ ስለመሆኑም አስታዉቋል፡፡
በተጨማሪም በኢትዮ-ሱዳን ድንበር ላይ በሱዳን ወታደሮች እና የአካባቢ ሚሊሻዎች ላይ በደረሰው ጉዳት ማዘኑን ገልጿል፡፡

በአባቱ መረቀ

ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply