ኢትዮጵያ ሁለት አዳዲስ ኤር ባስ የጭነት አውሮፕላኖችን ተረከበች። ዛሬ ኢትዮጵያ ሰዎችን ጨምሮ የሸቀጣሸቀጥ አና ለተለያዩ እቃዎች የጭነት አገልግሎት የሚሰጡ ሁለት አዳዲስ የካርጎ…

ኢትዮጵያ ሁለት አዳዲስ ኤር ባስ የጭነት አውሮፕላኖችን ተረከበች።

ዛሬ ኢትዮጵያ ሰዎችን ጨምሮ የሸቀጣሸቀጥ አና ለተለያዩ እቃዎች የጭነት አገልግሎት የሚሰጡ ሁለት አዳዲስ የካርጎ አውሮፕላኖችን ተረክባለች።

አውሮፕላኖቹ በፈረንሳዩ ቱሉዝ ኤርባስ ካምፓኒ ሰራሽ የሆኑ A-350 የተሰኙ ሲሆን ከ 150 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ እንደተደረገባቸው ተገልጿል።

በአቪዬሽን ዘርፍ ቺፍ ኦፕሬቲን ኦፊሰር የሆኑት እና አውሮፕላኖቹን የተረከቡት መስፍን ጣሰው እንደተናገሩት፣ እነዚህ አውሮፕላኖች ከሶስት አመት በፊት ኤርባስ ከተባለ የፈረንሳይ አውሮፕላን አምራች ካምፓኒ ጋር እንዲመረቱ ባደረግነው ውል መሰረት አሁን ሙሉ ምርታቸው አልቆ መረከብ ችለናል ብለዋል።

በተለይ የእነዚህ አዎሮፕላኖቻችን መምጣት በአለም አቀፍ ደረጃ ያለንን ጠንካራ አገልግሎት የበለጠ በማላቅ፣ ሀገራችን ከሌሎች አለማት ጋር የምታደርገውን የንግድ እንቅስቃሴዎችን ያቀላጥፋሉ ብለዋል።

እንደ ኦፍሰሩ ከሆነም አሁን በሀገራችን እነዚህን አዲስ አውሮፕላኖችን ጨምሮ 16 የሚሆኑ አውሮፕላኖች በስራ ላይ ያሉ ሲሆን በቀጣይም በቅርብ አመታት ውስጥ የሚመረቱ ወደ ስምንት የሚሆኑ ተመሳሳይ አውሮፕላኖችን ለማስመጣት እንቅስቃሴ ጀመረናል ብለዋል።

እነዚህ ኢዲስ አውሮፕላኖች በመጀመሪያ በረራቸው ለጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሚሆኑ ዊልቸሮችን ጨምሮ በርካታ የህክምና ቁሳቁሶችን እና የ አይሲቲ እቃወችን ይዘው ዛሬ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ደርሰዋል።

በጅብሪል ሙሀመድ
ጥቅምት 28 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply