ኢትዮጵያ ለሱዳን የምትሸጠው የሃይል አገልግሎት እንደማታቋርጥ አስታወቀች፡፡ሱዳን ጎረቤት ሀገር በመሆኗ ምክንያት ከኢትዮጵያ የምታገኘውን ሃይል ሙሉ በሙሉ ማቋረጥ አልተቻለም – ሲል…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/RJI-dqFY6rjlqEu6hAsagJLA1DnN60f2JMBTIMjZujNabDbETk8sCEsMPBL5oou472XRMW2DlPqr33yWHy-aMhsuJlUsDW2oUsW4JVGGnAnBz2Vyox9fMMwbFBekPZqwwXTBCA2gpXOpmHqwd2lA7G_i2HsunxVZ753qO0qypairsAgDVJZwHqXzU5Xov1Sn9aJ5ahFfXUPjeDKjgWmDtKU7RObm4qHbt-kC6im-sIN2lFOC9gBdXZOXL5LWCfae89f-1gEhIKGF1AVgp4QGUg4kX1T08dWU4hHMUvL9I99ddqrZs01-kf2B3RJIrwBQDca1S2uoJd652wfWyR8Dxw.jpg

ኢትዮጵያ ለሱዳን የምትሸጠው የሃይል አገልግሎት እንደማታቋርጥ አስታወቀች፡፡

ሱዳን ጎረቤት ሀገር በመሆኗ ምክንያት ከኢትዮጵያ የምታገኘውን ሃይል ሙሉ በሙሉ ማቋረጥ አልተቻለም – ሲል የኢትጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አስታውቋል፡፡

ሱዳን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አገልግሎት የወሰደችውን የሀይል አገልግሎት ክፍያ እስካሁን እንዳልፈፀመች፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል አገልግሎት ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ሞገስ መኮንን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ሃላፊው እንደገለጹትም ሱዳን ጎረቤት ሀገር በመሆኗ ምክንያት እንዲሁም ሃገሪቱ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ከኢትዮጵያ የሚደርሳትን የሃይል አቅርቦት ሙሉ በሙሉ ማቋረጥ እንዳልተቻለ ተገልጿል፡፡

የህዘብ ግንኙነት ሃላፊው ለሱዳን እስከ መቶ ሜጋ ዋት የሚደረስ ሃይል ይቀርብ እንደነበር አንስተው አሁን ላይ አቅርቦቱ በግማሽ እንደተቋረጠም ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከሽያጩ ማግኘት ከሚገባት ምን ያህል ገንዘብ አጣች ለሚለው ጥያቄም ሃላፊው ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡

ሱዳን ከኢትዮጵያ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት ያላት ሲሆን በቅርቡ በዓመት ጊዜ ውስጥ ለሱዳን ከተሸጠ የኤሌክትሪክ ኃይል ብቻ ከ54.6 ሚልየን ዶላር በላይ ገቢ ማስገባት ተችሎ ነበር፡፡

በለአለም አሰፋ

የካቲት 27 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply