ኢትዮጵያ ለ13 አመታት አንድም ቅርስ አላስመዘገበችም ተባለ፡፡

የቱሪዝም ሚኒስቴር የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረበበት ወቅት እንዳስታወቀው ላለፉት 13 አመታት ሃገሪቷ አንድም ቅርስ ማስመዝገብ አልቻለችም ብሏል፡፡

ሚኒስቴር መስራቤቱ ባደረገው ጥረትም ከ2014 ወዲህ 3 ቅርሶች መመዝገባቸውን ነው የተገለጸው፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናንሲሴ ጫሊ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ በየአመቱ አንድ ቅርስ ብቻ ነው ማስመዝገብ የምትችለው ብለው ለ13 አመታት ግን ቅርስ የሚባል ነገር በስማችን አልተመዘገበም ብለዋል፡፡

ሃገሪቱ ያላትን የቱሪዝም ፀጋዎችና የልማት ዕድሎች በመረዳት ቱሪዝም ለኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ለማህበራዊ ለውጥ የሚያበረክተውን አስተዋጽዖ በመረዳት የቱሪዝም ዘርፉ የመንግስትን ትኩረትና ቁርጠኝነት ያገኘ መሆኑን ገልፀዋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

ግንቦት 13 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply