ኢትዮጵያ ሱዳን በችግር ላይ እያለች መሬቷን ማስመለስ እንደማትፈልግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ አስታወቁ፡፡በወቅጣዊ የሱዳን ቀዉስና በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዙሪያ ማብራሪያ የሰጡት ጠቅ…

ኢትዮጵያ ሱዳን በችግር ላይ እያለች መሬቷን ማስመለስ እንደማትፈልግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ አስታወቁ፡፡

በወቅጣዊ የሱዳን ቀዉስና በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ዙሪያ ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሱዳን በችግር ጊዜ ዉስጥ እያለች ኢትዮጵያ የተወሰደባትን መሬት ማስመለስ አትፈልግም ነዉ ያሉት፡፡

ኢትዮጵያ ብትፈልግ የተወሰደባትን መሬት በሰዓታት ዉስጥ ማስመለስ እንደምትችልም አንስተዋል፡፡
ነገር ግን ኢትዮጵያ ለጎረቤቶቿ ክፉ የምታስብ ሀገር አይደለችም ነዉ ያሉት በማብራሪያቸዉ፡፡

የሰሜኑ ጦርነት መጀመርን ተከትሎ የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን መሬት መቆጣጠሩ የሚታወስ ነዉ፡፡

በአባቱ መረቀ
ሰኔ 27 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply