ኢትዮጵያ ስድስት ሺህ ሃኪሞችን ወደ ሥራ ታስገባለች

ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት ከመደበኛ የመንግሥት ቅጥር ውጭ ከስድስት ሺህ በላይ ሀኪሞችን ለመቅጠር መዘጋጀቷን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በርካታ ቁጥር ያላቸው የህክምና ባለሙያዎች ከሥራ ውጭ ሆነው እንደሚገኙ መረጃዎች ያሳያሉ።

በአዲሱ የፈረንጆች 2022 ዓመት ከአጋር ድርጀቶችና ከፌዴራል መንግሥት ተገኝቷል በተባለ ድጋፍ አዲስ ተመራቂ ሀኪሞችን ወደ ስራ ለማስገባት እየተዘጋጀ መሆኑን የጤና ሚኒስቴሩ አመልክቷል።

የመርኃግብሩ ዓላማ ህብረተሰቡ ጥራቱን የጠበቀ የጤና አግልግሎት እንዲያገኝና በብዙ ወጪ የሠለጠነ የሰው ኃይል እንዳይባክን የታለመ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ገልፀዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply