ኢትዮጵያ ቀጣናዊ ሰላሟን ለማስጠበቅ እና በድንበር አካባቢዎች ላይ ምንም አይነት የፀጥታ ችግር እንዳይፈጠር በትኩረት እየሰራች መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበር አካባቢ የሱዳን ሚሊሻዎች እና ወታደሮች ተኩስ መክፈታቸው ይታወቃል፡፡በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ መንግስት ትኩረቱን በሰሜን የአገሪቱ ክፍል በህግ ማስከበር ዘመቻ ላይ ነው ያደረገው በሚል የሱዳን ሚሊሻዎች ጥቃት ለመፈፀም መሞከራቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውሷል፡፡ይሁን እንጂ መሰል የድንበር አካባቢ የፀጥታ ችግሮች እንዳይስተዋል ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የሚኒስትሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡አምባሳደሩ አክለውም የሀገሪቱን ሰላም እና ፀጥታ ለማስጠበቅ ከሚደረገው የህግ ማስከበር ስራ ባሻገር ቀጣናዊ ሰላምን ለማስፈን የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲዊ ግንኙነትን አጠናክረናል ብለዋል፡፡

***************************************************************************

ቀን 12/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply