ኢትዮጵያ በሯን ለስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ክፍት ብታደርግም የሚደረግላት የገንዘብ ድጋፍ ግን እየቀነሰ መምጣቱን አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ የሚ…

ኢትዮጵያ በሯን ለስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ክፍት ብታደርግም የሚደረግላት የገንዘብ ድጋፍ ግን እየቀነሰ መምጣቱን አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡

ኢትዮጵያ በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ የሚተገበሩ አዳዲስ ቃልኪዳኖችን ጄኔቫ፣ ስዊዘርላድ በተጀመረው ዓለም አቀፍ የስደተኞች ጉባኤ (Global Refugee Forum) ላይ አቅርባለች፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት በስደተኞች እና ስደተኛ ተቀባይ ማህበረሰቦች ላይ የሚያተኩሩ ስድስት አዳዲስ ቃልኪዳኖች ጄኔቫ፣ ስዊዘርላንድ በተጀመረው 2023 ዓለም አቀፍ የስደተኞች ጉባኤ ላይ ለውይይት እየቀረቡ ነው።

ዓለም አቀፉ የስደተኞች ጉባኤ በየአራት ዓመቱ ስደተኞችን የሚደግፉ ሀገራት እና ዓለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች በተገኙበት ይካሄዳል።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን የተመራ ሚኒስትሮችና ሚኒስትር ዲኤታዎች የተካተቱበት የኢትዮጵያ ልዑክም በዓለም አቀፍ የስደተኞ ጉባኤ ላይ እየተሳተፈ ይገኛል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በመድረኩ ላይ ንግግር አድርገዋል።

በንግግራቸውም ኢትዮጵያ ለስደተኞች ዘላቂ ከለላ እና መፍትሔ የሚሰጥ ተራማጅ ፖሊሲ እንዳላት አንስተዋል፡፡

ምንም እንኳ በየጊዜው እየቀነሰ የመጣ የገንዘብ ድጋፍ ቢኖርም፣ ዓለም አቀፋዊ ኃላፊነትን በመጋራት መርህ አሁንም ለአዳዲስ ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች በሯን ክፍት አድርጋ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

ከልዑካን ቡድኑ አባላት በሥራና በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በትምህርት፣ በጾታ እኩልነትና ጾታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች መከላከልና ምላሽ ዙሪያ ኢትዮጵያ የምትገባቸውን ቃልኪዳኖች ቀርበዋል።

እስከ ነገ አርብ በሚኖረው ጉባኤ በአካባቢ ጥበቃ፣ በኃይል አቅርቦት፣ በመንገድ፣ በውሃ፣ በትምህርት፣ በጤናና በአካባቢ ንጽህና መሠረተ ልማቶች ማሻሻል እና በዲጂታል መሠረተ ልማት ዙሪያ አዳዲስ ቃልኪዳኖች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ መንግስት የስደተኞችንና የስደተኛ ተቀባይ ማህበረሰቦችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ተጨማሪ ፈንድ ለማግኘት የሚያስችለው ቃል-ኪዳን ቀደም ሲል በሀገር አቀፍ ደረጃ ሚኒስትሮችና ከፍተኛ የመንግስት ባልስጣናት በተገኙበት ውይይት ተደርጎበት የፀደቀ መሆኑ የሚታወስ ነው።

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ታህሳስ 04 ቀን 2016 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply