ኢትዮጵያ በሱዳን በጦርነት ቀጠና ውስጥ ያሉ ዜጎቿን እያስወጣች መሆኑን ገለጸች፡፡የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሱዳን መዲና ካርቱም ጨምሮ ሌሎች የጦርነት ቀጠና በአስቸጋሪ ሁኔታ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/MLjKj4xuhvKIDTcABgyk29TVXQLEop4FNBP2VpUJ0sodzoZujRAEfy7BHX6kmoyBnmMpL-ZvxPVl_JIGd8SMUwOIEo_WlV_Aux6U19iwOvVKjvV7nZoLAChFIDLp2KLtDkdlYXTRNMlPWWVa-Ol7AKQn8jIDEPEwD_l19_n18ere49RmZxe6nV6HJsy0byG3EvOJXn2kpyJt14GWcW2-1VNu_sM1gUqPBMdN3m9bOI1a7qecojMis074OsnI-s76DjHDfcuFYtPxWDbnJaMfvirUIpq7DEh8ABdiCvPfMmGTgX7hMefzg0_vpTJmtDzTPQ_Mnv7ZYc56T1uynxUt9g.jpg

ኢትዮጵያ በሱዳን በጦርነት ቀጠና ውስጥ ያሉ ዜጎቿን እያስወጣች መሆኑን ገለጸች፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሱዳን መዲና ካርቱም ጨምሮ ሌሎች የጦርነት ቀጠና በአስቸጋሪ ሁኔታ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያዊያንን የማስወጣት ስራ መቀጠሉን ገልጿል።

ይህንኑ የማስወጣት ሥራ እያስተባበረ ያለው በብሔራዊ ደረጃ የተቋቋመው ግብረ-ኃይል ዓርብ ጥቅምት 23 ቀን 2016 ዓ.ም ተመላሾችን ያሳፈሩ አራት አውቶቡሶችን ከካርቱም በመተማ በኩል ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ አድርጓል።

የተቋቋመው ብሔራዊ ግብረ ኃይል ተመላሾች ወደ የቤተሰቦቻቸው እስኪደርሱ ድረስ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ከአሁን በፊት ቁጥራቸው ከ34 ሺህ 700 በላይ ኢትዮጵያውያን ከጦርነት ቀጣና ወጥተው ወደ ሀገራቸው መግባታቸው ይታወሳል።

በአባቱ መረቀ

ጥቅምት 26 ቀን 2016 ዓ.ም

ለታማኝና ወቅታዊ መረጃዎች ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8
YouTube
https://www.youtube.com/…/UCn4D20GPsAtNqN5bIC1BhFA/video

Source: Link to the Post

Leave a Reply