ኢትዮጵያ በሶማሊያ ሞቃዲሾ የተፈጸመዉን ጥቃት አወገዘች፡፡ኢትዮጵያ በሶማሊያ ሞቃዲሾ በጀነራል ጎርዶን የጦር ሰፈር የተፈጸመዉን ጥቃት አወገዘች፡፡ቅዳሜ ዕለት በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ በጦር ሰፈ…

https://cdn4.cdn-telegram.org/file/m55MZGbeE7XcCEMR2KRFXDVQaQOa8UHtqLvzmL4mB35QEug5VzzLI6OwpTx7v_u4fOCLhlvkUpm79hZF03Q_Nx9-Fk_BX70R3SZK0IMsRSPRA4xQcAhEXQpaeDZzzvJcgyLL2b9OOijGCoepZcqBZZKQXSaoxfUjQTosr1zvUImiA5avj3jb4pvCVO6wU8NofMcSHxf29qPWpMe-2qv_SjnqGvz_8Rf39br2mauWwQfwcAi1mlAUDBkdDB8vROosZ2646KG1Qc15ICTqGB3NRvwstA84tcnx8zGcSBaWWUt9MtKeQPH9u4XaYojsc0m84UM3UcZQMqcuBSRFZ9MiNA.jpg

ኢትዮጵያ በሶማሊያ ሞቃዲሾ የተፈጸመዉን ጥቃት አወገዘች፡፡

ኢትዮጵያ በሶማሊያ ሞቃዲሾ በጀነራል ጎርዶን የጦር ሰፈር የተፈጸመዉን ጥቃት አወገዘች፡፡

ቅዳሜ ዕለት በዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ በጦር ሰፈሩ ወታደራዊ አዛዦች ላይ ኢላማ ያደረገዉን ጥቃት እንደምታወግዝ ነዉ የገለጸቸዉ፡፡

አዲሱ የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀ ስላሴ ጥቃቱ በሽብርተኝነት ምክንያት በቀጣናዉ ሰላም እና ደህንነት ላይ የተጋረጠዉን ስጋት የሚያሳይ ነዉ ብለዋል፡፡

አምባሳደር ታዬ በጥቃቱ ህይወታቸዉ ላለፉ ወታደሮች ቤተሰቦች፣ እንዲሁም ለሶማሊያ ህዝብ እና መንግስት የተሰማቸዉን ጥልቅ ሃዘን የኢትዮጵያን መንግስት እና ህዝብ በመወከል ገልጸዋል፡፡

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መከላከያ ይፋ እንዳደረገዉ 3ት ወታደሮቹ እና አንድ የባህሬን ወታደር በሽብር ጥቃቱ ህይወታቸዉ ማለፉን አስታዉቆ ነበር፡፡

የአልሸባብ ታጣቂዎች ደግሞ ለጥቃቱ ሃላፊነትን ወስደዋል፡፡

እስከዳር ግርማ

የካቲት 06 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply