
#ኢትዮጵያ በተፈናቃዮች ብዛት ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት #በሁለተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ እንድ ጥናት አመላከተ ግንቦት 03 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በ2022 ኢትዮጵያ በተፈናቃዮች ብዛት ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን በማስቀደም በሁለተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ የኖርዌ የስደተኞች ካውንስል የተፈናቃዮች ክትትል ማዕከል አስታወቀ፡፡ … ማዕከሉ ይፋ ያደረገው የ2022 አመታዊ መረጃ እንደሚያሳየው በኢትዮጵያ አጠቃላይ ተፈናቃዮች ቁጥር ሁለት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ አምስት ሺ መሆኑን አስታውቋል። ከዚህ ውስጥ ሁለት ሚሊዮን 32 ሺ የሚሆኑት የተፈናቀሉት በ #ግጭት እና #ብጥብጥ ምክኒያት መሆኑም ተገልጧል፡፡ በኢትዮጵያ በድርቅ ሳቢያ ብቻ በ2022 ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 686ሺ መሆኑን የጠቆመው ማዕከሉ በተለይም #በኦሮምያ እና #ሶማሌ ክልሎች ሁኔታው የከፋ መሆኑን አስታውቋል፤ በሁለቱ ክልሎች ከድርቁ በተጨማሪ ግጭት እና ሁከት ጉዳት እንዳደረሰባቸው አመላክቷል። @ addis standard ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post