ኢትዮጵያ በታጣቂዎች እገታ ከሚፈጸምባቸው የዓለም ቀዳሚ አገራት መካከል መመደቧ ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 27 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የታጋቾች…

ኢትዮጵያ በታጣቂዎች እገታ ከሚፈጸምባቸው የዓለም ቀዳሚ አገራት መካከል መመደቧ ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መጋቢት 27 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የታጋቾችን ሰብዓዊ መብት ከማስከበር ጋር በተያያዘ ጥናት ያደረገው ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ፣ ኢትዮጵያ ከመንግሥታዊ የጸጥታ ኃይሎች ውጭ በታጣቂ ኃይሎች እገታ ከሚፈጽምባቸው ቀዳሚ አገራት መካከል አንዷ መሆኗን አስታውቋል፡፡ ኮሚቴው በጥናቱ 80 ታጣቂ ድርጅቶች ያገቷቸው በአስር ሺሕ የሚቆጠሩ ታጋቾች ያሉበት ሁኔታ የተመለከተ ሲሆን፣ ለታጣቂ ቡድኖች የታጋቾችን አያያዝ በተመለከተ ምክረ ሀሳቦችን ማቅረቡን አስታውቋል፡፡ በርካታ ታጋቾች ካሉባቸው አገራት መካከል ኮንጎ፣ ሶሪያ፣ ኮሎምቢያና ኢትዮጵያ ዋነኞቹ ናቸው ተብሏል። በኢትዮጵያም ትግራይ ክልል በታጣቂ ኃይሎች እገታ የሚከናወንበት መሆኑ በልዩነት ተነስቷል፡፡ በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል የሚንቀሳቀሰው ራሱን የኦሮሚያ ነጻነት ሰራዊት ብሎ የሚጠራውና በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው ሸኔ በርካታ እገታዎችን በመፈጸም ይታወቃል። በኢትዮጵያ ከውጊያዎች ባለፈም ግለሰቦችን በማገት ገንዘብ ለማግኘት የሚደረጉ ጥረቶች እንዳሉም ይታወቃል፡፡ አዲስ ማለዳ እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply