ኢትዮጵያ በአለም ሶስተኛዋ የቤት ዋጋ አይቀመሴ ከሆነባቸው ሃገራት መካከል ተቀመጠች፡፡ ቢዝነስ ኢንሳይደር አፍሪካ ባወጣው የቤት ዋጋ ማነጻጸርያ ኢትዮጵያ ለዜጎቿ በውድ ወጋ ቤት ከሚያቀርቡ ሃ…

ኢትዮጵያ በአለም ሶስተኛዋ የቤት ዋጋ አይቀመሴ ከሆነባቸው ሃገራት መካከል ተቀመጠች፡፡

ቢዝነስ ኢንሳይደር አፍሪካ ባወጣው የቤት ዋጋ ማነጻጸርያ ኢትዮጵያ ለዜጎቿ በውድ ወጋ ቤት ከሚያቀርቡ ሃገራት መካከል ሶስተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧታል፡፡

ከአፍሪካ ካሜሮን እጅግ ውድ በተባለ ዋጋ ለዜጎቿ ቤት ከሚያቀርቡ ሃገራት መካከል በአንደኛ ደረጃ ተቀምጣለች፡፡

ቢዝነስ ኢንሳይደር አፍሪካ ባወጣው ትንትና በዓለም ላይ የቤት ዋጋ ማነጻጸሪያ ስሌት በሚሰራው ሰርቢያዊው የመረጃ ሰብሳቢና ተንታኝ Nembeo ባቀረበው የዋጋና የገቢ ስሌት መሰረት ሀገራችን በዓለም ሶስተኛዋ የቤት ዋጋ አይቀመሴ የሆነባት ሃገር መሆኗን አስቀምጧል፡፡

በስሌቱ ላይ በዚህ ወር በፈረንጆቹ 2024 ላይ የሃገራችንን የነፍስ ወከፍ ገቢ 2ሺህ 221 የአሜሪካ ዶላር አድርጎ የወሰደ ሲሆን የቤቶች ዋጋን በካሜ በመሃል ከተማ 2ሺህ154 ዶላር ከከተማ ውጪ 1ሺህ 271አድርጎ የወሰደ ሲሆን ለስሌቱም አማካኝ ዋጋን የወሰደ ሲሆን እንደ ቤተሰብ ገቢ የነፍስ ወከፍ ገቢውን በ1.5 በማባዛት ተጠቅሟል።

ለሁሉም ስሌቶች አማካኝ የቤት ስፋትን 90ካሬሜ እንደሚጠቀም የአሰላሉ አካሄድ ላይ አትቷል።

ነገር ግን በግብይትና በዘርፉ ውስጥ እንዳለ ሰው ታሳቢ የተደረጉት በዋጋ አነስተኛ ሲሆን በመሃል ከተማ ከ 2ሺህ 800 ዶላር በላይ ሲሆን ከከተማ ውጪ 1ሺህ 700ዶላር አካባቢ ይሆናል ይህ ኮንዶሚኒየምን ጨምሮ የተሰላ ነው ተብሏል፡፡

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
ጥር 17 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።
Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply