ኢትዮጵያ በአዉሮፓ ህብረት የገንዘብ እገዳ ምክንያት የሳታላይት መፈብረኪያ እና መገጣጠሚያ ማዕከል ግንባታ መጀመር አልቻለችም ተባለ፡፡የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለኢትዮ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/RdbmqUsjwM5t_y04ZT8EW4F-ymx_ztvwCHoZ9bv9fVcgg5QnSPm9z5_QuAP409m-pwHW0GJ14lRJwa4hkV9gs8XJrShbEJzUFg4ifBW0ONW7oJA0EekD3LeQSzcww1P548e6lotbosRUpCC_t8mUOLgrUs-DM7fOnkE4e9wnJ4Xk2vmSQcjhoCG20AQ1k6Y5CgohSrKlv5S6GiZREP-5G_0nkYUEw3dtZ-Mo4SwzyJh9yfxRz6sUaY_NxGt97EJjKeiButVDjo_Zox_QoFF--u01xWyAweFyDrQX_HvHZeUbjItSPu94ZvE2H_BesSlNn6X5t_qa0g1E84BWCot2tg.jpg

ኢትዮጵያ በአዉሮፓ ህብረት የገንዘብ እገዳ ምክንያት የሳታላይት መፈብረኪያ እና መገጣጠሚያ ማዕከል ግንባታ መጀመር አልቻለችም ተባለ፡፡

የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀዉ፣ ሳተላይትን በአገር ዉስጥ መፈብረክ የሚያስችል ኤ አይቲ የተሰኘ ፕሮጀክት የአዉሮፓ ህብረት ገንዘቡን ባለመልቀቁ መጀመር አልተቻለም ብሏል፡፡

ፕሮጀክቱ እስከ 50 ሚሊዮን ዩሮ ወጪ የሚጠይቅ ሲሆን የፈረንሳይ መንግስት እና የአዉሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ድጋፍ ለማድረግ ከ2 አመት በፊት ተስማምተዋል ተብሎ ነበር፡፡

ይሁን እንጅ ለጋሾቹ ገንዘቡን ባለመልቀቃቸዉ የማእከሉን ግንባታ ማስጀመር እንዳልተቻለ፣ የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ምክትል ዳይሬክተር ዶክተር የሽሩን አለማየሁ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡
ይህ ፕሮጀክት ሳተላይትን በአገር ዉስጥ መፈብረኪያ፣ መገጣጠሚያ እና መፈተሻ ማዕከል እንደሆነም ሲነገር ቆይቷል፡፡

ኢትዮጵያ ከአገረ ቻይና ያመጠቀቻት ሳተላይት 70 ኪሎ ግራም እንደምትመዝን ይታወቃል፡፡
በአገር ዉስጥ የሚገገነባዉ የቴክኖሎጂ ማዕከል ግን 500 ኪሎ ግራም የሚመዝኑ ሳተላይቶችን ማምረት የሚችል መሆኑም ተነግሮ ነበር፡፡
ኢትዮጵያ ያመጠቀቻት ሳተላይት ሀገር ውስጥ ለመስራት እንዲሁም ከኢትዮጵያ ለማምጠቅ የሚያስፈልገው ቴክኖሎጂና የሰው ሀይል ባለመኖሩ ወደ አገረ ቻይና ድጋፍ ለማግነት መሄዷ የሚታወስ ነዉ፡፡

በአባቱ መረቀ

ነሐሴ 09 ቀን 2014 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply