ኢትዮጵያ በኦነግ ኬኛ ፈንጂ ወረዳ! የኦሮሙማ ብሔራዊ የጋራ ኃብታችን ውርስና ስልቀጣ? (ክፍል 1) ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ)

ኢትዮጵያ በኦነግ ኬኛ ፈንጂ ወረዳ! የኦሮሙማ ብሔራዊ የጋራ ኃብታችን ውርስና ስልቀጣ? 

Ethiopia under OLF Minefield! Where to Invest?  (ክፍል 1)  ፀ/ት ፂዮን ዘማርያም (ኢት-ኢኮኖሚ)

ኢትዮጵያ በኦነግ የኬኛ ፈንጂ ወረዳ!›› የኦሮሙማ ብሔራዊ የጋራ ኃብታችንን ውርስ?

ብሔራዊ የጋራ ሃብታቸንን ለመውረስ ደፋ ቀና በማለት ላይ ይገኛል? የማዕድን ኃብት ግኝት እርግማን አስከትሎል፡፡ ሃዘን ያዘንባል! በኦሮሙማ የፈንጂ ወረዳ ንፁሃን ዜጎች ይታረዳሉ፣ ሃብትና ንብረታቸው ይዘረፋል፣ይሰደዳሉ !!!

የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ፣ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ፣የወርቅ ማዕድናችን፣ የማዕድን ኃብታችን፣ ለአብነት የሚጠቀሱት የኢትዮጵያውያን ብሔራዊ የጋራ ሃብታቸን ናቸው፡፡ የኦሮሙማ ብሔራዊ የጋራ ሃብታቸንን ለመውረስ የነደፈው የፖለቲካ ሴራ ምን ይመስላል? በሃገራችን ውስጥ የሚገኙ የባህር ማዶ ኢንቨስተሮች እነማናቸው? የኢትዮጵያውያን ብሔራዊ የጋራ ሃብታቸን ከኦነግ ኬኛ ፖለቲካ እንዴት እንጠብቅ? ለኢትዮጵያ አበዳሪ አገሮችና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ፍላጎትና የሚያሳድሩት ተፅዕኖ እንደት ይታያል? ኢትዮጵያ ብድር ስትበደር ቦይንግ አይሮፕላኖቾን በኮላተራል እንደምታስይዝ ስንቶቻችን እናውቃለን፡፡ የውጪ እዳ መክፈል ካልቻልን አየር መንገዳችንን፣ ኢትዮቴሌኮም፣ የምድር ባቡር፣ ግድባችንንም በአበዳሪዎቻችን ሊወሰድ እንደሚችል ማወቅ ይኖርብናል፡፡ የሃገራችን የውጭ ዕዳ ሃምሳ አራት ቢሊዮን ዶላር ደርሶል፡፡ ሃገራችን ሹማምንት ከውጭ ሃገር እየተበደሩ ይገነባሉ እዳቸውን ግን አይከፍሉም፡፡ አሁንም ሌላ ብድር፣ ያለአንዳች ጥናት ሌላ ብድር በዘመነ አብይ አህመድ አገዛዝም ቀጥሎል፡፡ መረጃውን እንሆ፡-

‹‹በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገነባው ግዙፍ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የግንባታ ቅድመ ዝግጅትን በተመለከተ በገንዘብ ሚኒስቴር ውይይት ተካሂዷል፡፡ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ከኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም ጋር በኢትዮጵያ ሁለተኛው ሜጋ ፕሮጀክት በሆነው አዲሱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የግንባታ ቅድመ ዝግጅት ላይ ያተኮረ ውይይት አካሂደዋል፡፡ በዚሁ ወቅት አዲሱ ፕሮጀክት የኢትዮጵያን የአውሮፕላን ማረፊያ አገልግሎት ወደ ከፍተኛ ደረጃ እንደሚያሻግር ተመላክቷል፡፡ ፕሮጀክቱ ተግባራዊ ሲሆን የኢትዮጵያን የአየር ትራንስፖርት ተጓዦች እና የካርጎ መናኸሪያ በማድረግ የላቀ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል ተብሏል፡፡ ለኢትዮጰያ ዘላቂ ልማትና እድገት ትልቅ ሚና እንደሚጫወትም ተስፋ ተጥሎበታል፡፡ በውይይቱ ወቅት ከዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያው በተጨማሪ በዕቅድ በተያዙ አምስት የአውሮፕላን ማረፊያዎች እና ተርሚናሎች የማስፋፋት ስራዎች መሰናዶ ላይ መግባባት ላይ መደረሱን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡››   (1)

{ሀ} የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ Ethiopian Airlines

የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ የአፍሪካን ትልቁን ዓየር መንገድ ለመስራት ማቀዱን አስታውቆል፡፡ ዓየር መንገዱ ይህን እቅዱን ለማሳካት አምስት ቢሊዮን ዶላር (ሁለት መቶ ቢሊዮን) ብር የግንባታ ወጪ ይጠይቀናል፡፡ የአዲሱን ዓየር መንገድ ትልቅ ኢንቨስትመንት እንደሆነ በቀላሉ ለመረዳት የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ አምስት ቢሊዮን ዶላር የግንባታ ወጪ ጋር እኩል መሆኑን በመገንዘብ ነው፡፡ አዲሱ ዓየር መንገድ በውድድር ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት፣ ብዙ መንገደኞችን በማስተናገድ ከደቡብ አፍሪካው ጆሃንስበርግ ዓየር ማረፍያ የበለጠ አገልግሎት መስጠት ይጠበቅበታል፡፡ (2)

Ethiopian Airlines Announces Plans to Build Africa’s Largest Airport (Video) /BY CAILEY RIZZO/

FEBRUARY 04, 2020/ Ethiopian Airlines is spending an estimated $5 billion to build the largest airport in Africa. It could also become Africa’s busiest airport, capable of handling more passengers than the current busiest hub in Johannesburg, South Africa.

የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የግንባታ ወጪ አምስት ቢሊዮን ዶላር ሲገመት የሚገኘውም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት መተከል ወረዳ— ውስጥ ነው፡፡ በ1983ዓ/ም በህወሓት ኢህአዴግ ዘመን በተፈጠረ አዲስ ጂኦፖለቲካ ካርታ ክልሉ ከጎጃምና ከወላጋ ክፍለግዛቶች ተቆርሶ የተመሠረተ አስተዳደር ነው፡፡ ግድቡ በእያንዳንዱ የኢትዮጵያ ህዝብ አንጡራ ኃብት በመዋጮ የተሠራ የሃገር ቅርስና የሁሉም ህዝብ አሻራ ያረፈበት የአንድነታችን የሳንባችን  እስትንፋስ፣ የልባችን የማያቆርጥ ትርታ ጉሰማ ከአንዱ ዜጋ ወደ ሌላው ዜጋ የሚተላለፍ ዘላለማዊ ምልክት በሃገራችን ምድር ላይ የታተመ የዱካና ኮቴችን የጋራ አሻራ ነው፡፡

የኢትዮጵያ አብሥራ ዓየር መንገድ፡- The Absera Airport

የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ የአይሮፕላኖች ማረፍያና ማኮብኮቢያ አዲስ ዓየር ማረፍያ ጣቢያ በደብረዘይት ከተማ  የግንባታ መርሃ-ግብር በዓየር መንገዱና በኦሮሚያ ክልል መንግሥት ስምምነት ተደርጎል፡፡ የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ

ማናጀር ተወልደ ገብረማርያም ዓየር መንገዱ የ2025 እኤአ አቅዶት የነበረውን ዓላማዎች ከሰባት ዓመት በፊት አስቀድሞ ተጠናቆል፡፡ በዚህም የተነሳ ዓየር መንገዱ አዲስ ራዕይ ወደ 2035 እኤአ በመዝለቅ አዲሱን የታላቆን የኢትዮጵያ ህዳሴ ዓየር መንገድ  ተሸጋግሮል፡፡

In an interview with the Ethiopian News Agency (ENA), Ethiopian Airlines CEO Tewolde Gebremariam said that the airline completed its 2025 goals seven years ahead of schedule. The airline is now moving onto its 2035 vision, which includes the massive new airport. Ethiopian Airlines is currently operating flights out of Bole International Airport in Addis Ababa, the country’s capital. “The airport looks very beautiful and large, but with the growth that we are [seeing] every year, in about 3 or 4 years, we are going to be full,” Gebremariam told ENA. That being said, they are moving ahead with building the airport, which they are calling Absera. The Absera Airport will take up about 13 square miles of land in the town of Bishoftu, almost 40 miles south of Addis Ababa. The airport will be able to accommodate about 100 million passengers per year.

የአብሥራ ዓየር መንገድ፡-  የቦሌ ዓለም አቀፍ ዓየር ማረፍያ በአዲስ አበባ ውብና ትልቅ ግንባታ ሲሆን በሦስትና አራት አመታት ውስጥ በሙሉ አቅሙ ደረጃ ላይ ይደርሳል ለዚህ ነው የአብሥራ የዓየር ማረፍያ ግንባታ ፡፡  የአብሥራ የዓይሮፕላን ማረፍያ ከአዲስ አበባ ከተማ አርባ ኪሎሜትር ርቀት በምትገኘው ብሸፍቱ ከተማ በአስራሦስት ስኩየር ማይልስ የተንጣለለ መሬት ላይ የሚገነባ ኤርፖርት ነው፡፡ ኤርፖርቱ ሲጠናቀቅ መቶ ሚሊዮን መንገደኞችን በዓመት ማስተናገድ ይችላል ተብሎ ይታመናል፡፡ የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲም በዘረኛነትና በተረኛነት ስሜት አዲስ አበባን ከተማ ዲሞግራፊውን ለመቀየር ‹‹ፊንፌኔ ኬኛ›› የፖለቲካ ሴራ ብዙ ንጹሃን ዜጎች ከከተማዋ ሲያፈናቅሉ ኮንዶሚኒየም ሲዘርፉ ተስተውለዋል፡፡ የኦዴፓ ብልፅግና የኦሮሙማ የመስፋፋት ፖሊሲና የዘር  ፍጅት በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ወንጀለኞች ፍርድ ቤት  ዶክተር አብይ አህመድና ሽመልስ አብዲሳ ለፍርድ መቅረባቸው አይቀርም እንላለን፡፡

 

{ለ} የታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ

የታላቁ የኢትዩጵያ ህዳሴ ግድብ ለሃገሪቱ የሚያስገኘው ገቢ ትንበያ (Revenue Projection) በግልፅ የተቀመጠ ጉዳይ ስለሆነየፕሮጀክቱ ጥቅምና ጉዳት (Cost-Benefit Analysis) ስሌት በጥናቱ መሠረት ካልተተገበረ የአዋጭነትና ትርፋማነት ጥናቱ ከንቱ ሆኖ ስለሚቀር የግድቡ ፕሮጀክት የድርድሩ ቀይ መሥመር ለመንግሥትና ለተደራዳሪዎች አይነኬ ውሃልኮችን ህዝብ እንዲያውቃቸው ማድረግ የምሁራን ኃላፊነት ነው እንላለን፡፡ የታላቁ የኢትዩጵያ ህዳሴ ግድብ፣  ከመጋቢት 24 ቀን 2003 እስከ መጋቢት 24 ቀን 2012 ዓ/ም የዘጠኝ  ዓመታት ጉዞና እውነታዎች ውስጥ፡-የሚያመነጨው የሃይል መጠን 6 ሺ 450 ሜጋ ዋት፣ ለመገንባት የሚያስፈልገው ገንዘብ መጠን 80 ቢሊዮን ብር (ከ4-5 ቢሊዩን የአሜሪካ ዶላር በላይ)፣የሃል ማመን ዩኒቶች ብዛት 16፣እንዳንዱ ዩኒት የሚያመነጨው የሃይል መጠን ከ 375 እስከ 400 ሜጋ ዋት፣ የዋናው ግድብ ከፍታ 145 ሜትር፣ የዋናው ግድብ ርዝመት 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር፣የዋናው ግድብ ውፍረት የግድቡ ግርጌ 130 ሜትር ሲሆን የግድቡ ቻፍ ወይም የላይኛው ክፍል 11 ሜትር፣ ግድቡ የሚይዘው የውሃ መጠን 74 ቢሊዩን ኪዩቢክ ሜትር፣ ግድቡ ሚሸፍነው የቦታ ስፋት 1 ሺ 680 ስኩዌር ኪሎ ሜትር፣ ሲጠናቀቅ ውሃ ሚተኛበት መሬት ርዝመት 246 ኪሎ ሜትር፣ ለግድቡ ግንባታ ከህዝብ ቃል የተገባ የገንዘብ መጠን 12 ነጥብ 8 ቢሊዩን ብር፣ ቃል ከተገባው እስካሁን የተሰበሰበ ገንዘብ ብዛት 9  ነጥብ 6 ቢሊዩን ብር፣ ግድቡን የጎበኙ ኢትጵያውን ብዛት 250 ሺ፣ ግድቡን የጎበኙ የውጭ ሚዲያዎች ብዛት 400 ደርሶል፡፡ በ2023 እኤአ 1 ቢሊዩን ዶላር በዓመት ለሃገሪቱ የውጪ  ምንዛሪ ከኤሌትሪክ ሃይል ሽያጭ  ያስገኛል ተብሎ ተተንቡዩል፡፡ (3)

የታላቁ የኢትዩጵያ ህዳሴ ግድብ በመጋቢት ወር 2003 ዓ/ም ሥራው ተጀመረ፣ የጥቁር አባይ ወንዝ 85 በመቶ ከናይል ወንዝ ድርሻ አለው፡፡ የህዳሴው ግድቡ 74 ቢሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውኃን ለመሙላት ከ4 እስከ 7 አመታት ውስጥ ይሞላል የሚል አቆም በኢትዮጵያ በኩል ተይዞል፡፡  በግብፅ በኩል ደግሞ ግድቡ ከ10 እስከ 21 ዓመታት ውስጥ ቀስ ብሎ እንዲሞላ ይሻሉ፡፡ የህዳሴው ግድብ ሲጠናቀቅ 6450 ሜጋዋት የኤሌትሪክ ኃይል በአመት ያመነጫል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የታላቁ የኢትዩጵያ ህዳሴ ግድብ ፕላን ሀ፡-  ከታላቁ የኢትዩጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክትን 6450 ሜጋዋት የኤሌትሪክ ኃይል በአመት ለማመንጨት 5 ቢሊዮን ዶላር የግንባታ ወጪ  በማውጣት 79 በመቶ በመጠናቀቅ ላይ ያለ ፕሮጀክት ነው፡፡ ግብፅና ኢትዮጵያ በግድቡ ሙሌት ላይ አልተስማሙም፡፡ ግብፅ በጦርነት ግድቡን ለመምታትና ፕሮጀክቱ ተግባራዊ እንዳይሆን በተደጋጋሚ ሳንካ ፈጥራለች፡፡ Negotiators are presenting this as a win-win for both Egypt and Ethiopia. There have been fears the countries could be drawn into war if it is unresolved.” ከታላቁ የኢትዩጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክትን የኤሌትሪክ አገልግሎት ወደ መስኖ ፕሮጀክትነት የመቀየር ጥናት አስፈላጊ ነው እንላለን፡፡ ከታላቁ የኢትዩጵያ ህዳሴ ግድብ ኃብትን የኢትዮጵያውያን አንጡራ ኃብትና ንብረት እንጂ የወያኔ፣ የኦነግ አሊያም የኦዴፓ ብልፅግና ኃብት ሊሆን አይችልም፡፡ ወያኔ ኢህአዴግ ግድቡ የሚገኝበትን ቢኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልን ለመጠቅለል ድንበር ለማስፋፋት አዲስ ካርታ በመስራት ሞክሮ ከሽፎበት ሩጫውን ጨርሶል፡፡    የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲም በዘረኛነትና በተረኛነት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ውስጥ የሚኖረውን አማራ ለማስወጣትና ዲሞግራፊውን ለመቀየር የፖለቲካ ሴራ ብዙ ንጹሃን ዜጎች ታርደዋል ተሰደዋል፡፡ የኦዴፓ ብልፅግና የኦሮሙማ የመስፋፋት ፖሊሲ የዘር  ፍጅት በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ወንጀለኞች ፍርድ ቤት  ዶክተር አብይ አህመድና ሽመልስ አብዲሳ ለፍርድ መቅረባቸው አይቀርም እንላለን፡፡

 

{} ኢትዮጵያ ከወርቅ ማእድን የውጭ ንግድ ገቢ ከ602 ወደ 30 ሚሊዮን ዶላር አሽቆልቁሎል ነበር፡፡

ብሔራዊ የጋራ ሃብታቸንን የት ኢንቨስት እናድርግ? የማዕድን ኃብት ግኝት እርግማን ያዘንባል! የፈንጂ ወረዳ!!!

ከማዕድን ሚኒስትሩ ከነበሩት ከቶሎሳ ሻጊ ሞቲ እስከ ታከለ ኡማ  ድረስ የኢትዮጵያ ማዓድን ኃብት እድገትና ማሽቆልቆል የፖለቲካ ሴራ የተጠናወተው የዘረኛና ተረኛ ስሜት በወያኔ ኢህአዴግ ኢዛና ወርቅ ማዕድን እንዲሁም ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ በለገደንቢ ወርቅ ማዕድን የኬኛ ፖለቲካ የተሳሰረ ነው፡፡

የወርቅ መዓድን በኢትዮጵያ  Gold mining in Ethiopia:-ያልነጠረ ብረት ክምችት የተጣራ የወርቅ ማዓድን የሚገኝ የወርቅ ቡችላ ከለገደንቢ(በደቡብ ኢትዮጵያ በሲዳሞ ጠቅላይ ግዛት  እና ሻኪሶ በግል ካንፓኒዎች የሚቆፈርና የሚዛቅ የወርቅ መዕድን ምርት እስከ አምስት ቶን በዓመት እንደሆነ የመረጃ ሪፖርት   ያሳያል፡፡

Large ore based gold mines are the Lega Dembi (the largest mine in the Sidamo province of southern Ethiopia) and Sakaro, which have been mined by private companies; the amount of gold produced by these mines is reported to be about 5 tons per year.

ሻኪሶ  Shakiso:-ሻኪሶ በደቡብ ኢትዮጵያ በኦሮሚያ ክልል በጉጂ ዞን የሚገኝ ከተማ ሲሆን ሁለቱ ትልልቅ የወርቅ ማዕድናት የለገደንቢ ወርቅና በሳውዲው ቱጃር የግል ኃብትነትና  የቀንጢቻ ታንታለም  በሳውዲ አረቢያ ፍላጎቸ ይዘወራል፡፡ ሌላው ደግሞ ትግራይ በስተ ሰሜን ኢትዮጵያ ኢዛና የወርቅ ማዕድን በአሜሪካ የወርቅ ማእድን ቆፋሪ ካንፓኒ ኒውሞንት ይዘወራል፡፡ የጣልያኖች ጥረት ከ1930 እኤአ ጀምሮ በወለጋ በቱሉ ካፒ የወርቅ አውጪ ካንፓኒ ጥናት የተገኘ 48 ቶን የወርቅ ማዕድን ኃብት በ2013 በመሠረቱን ሳይፕረስ ባደረገው የወር ማዕድን አውጪዎች ቡድን ኬኢኤፍአይ ወርቅ አውጪዎች በ2.3 ቢሊዮን ዶለር ወይም 1.7 ቢሊዮን ፓውንድ የገበያ ዋጋ እሴት እንዳለው ይገመታል፡፡

Shakiso is a town in southern EthiopiaLocated in the Guji Zone of the Oromia Region, this town has a latitude and longitude of 5°45′N 38°55′E and an elevation of 1758 meters above sea level. Two of the major mines of Ethiopia are located near Shakiso: the Lega Dembi gold and the Kenticha tantalum mines.One is at Lega Dembi slightly to the east, owned by Saudi interests. The other, at Tigray in the north of the country, is owned by American mining giant Newmont, and just started production late last year. More is already on the way: the beneficiary of the Italian efforts from the 1930s in Welega is the Tulu Kapi gold prospect, containing 48 tonnes of gold. This was most recently acquired in 2013 by Cyprus-based mining group KEFI Minerals (market value: roughly US$2.3 billion (£1.7 billion)).

የግብጽ ካንፓኒ ብዛት ያለው የወርቅ ማዕድን ክምችት በኢትጵያ አገኙ (Egyptian company discovers largest gold reserve in Ethiopia/March 22, 2014

የግብጽ ካንፓኒ አስኮም (Ascom Precious Metals Mining) የተባለ ካንፓኒ ብዛት ያለው የወርቅ ማዕድን ክምችት በኢትጵያ በደቡብ ምስራቅ፣  በቢኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ በ2010 እኤአ ማግነቱን አስታውቀው ነበር፡፡ የማዕድን ሚኒስቴር የነበሩት ቶሎሳ ሻጊ የወርቅ  ማዕድን መገኘቱን ለሪፖርተር በደስታ ገልጸው ነበር፡፡ በ2016እኤአ የግብፁ ካንፓኒ አስኮም በአሶሳ ዞን ብዛት ያለው የወርቅ ማዕድን  ክምችት አርባ ስምንት ቶን እንደሚሆን ገልጸው ነበር፡፡ በሃገረ ኢትዮጵያ የወርቅ ማዕድን ኃብት ከቡና ምርት ቀጥሎ በዓለም አቀፍ የውጪ ንግድ  የውጪ ምንዛሪ እስከ ስድስት መቶ ሚሊዮን ዶላር የሚያስገኝ ሲሆን  ከዚህ ውስጥ ዘጠና በመቶ ከወርቅ ማዕድን  ገቢ ይገኛል፡፡ የሜድሮክ ጎልድ ካንፓኒ አራት ቶን ወርቅ በዓመት በማምረት ሲውዘርላንድ ሃገር ይሸጣል፡፡ የሜድሮክ በሳካሮ አዲስ የወርቅ ማዕድን ቦታ አግኝቶል፡፡ “Addis Ababa, Ethiopia – An Egyptian company, Ascom Precious Metals Mining, has discovered what is said to be the largest gold ore reserve ever discovery in the history of gold exploration in Ethiopia. The discovery is made in the Benishangul Gumuz Regional State, in south- west Ethiopia. Ascom has been prospecting for gold and base metals in the Benishangul region since 2010. Two weeks ago Ascom made a presentation to senior officials of the Ministry of Mines about the new discovery. Tolossa Shagi Moti, Minister of Mines, told The Reporter that the ministry was happy with the discovery. “This is the largest gold discovery ever made in the country,” Tolossa said. As for Asosa, the Egyptian company ASCOM made a significant gold discovery in the zone in 2016. It published a maiden resource statement that claimed the presence of – curiously the same number – 48 tonnes of gold. Yet this only looks like the beginning. Gold has become Ethiopia’s major foreign currency earner next to coffee. The country earns more than 600 million dollars from mineral exports and gold contributes 90 percent of the earning. To date, MIDROC Gold is the only company engaged in large-scale mining. MIDROC annually exports four tons of gold, mainly to Switzerland. MIDROC Gold has discovered a new gold reserve in the Sakaro locality.”

የግብጽ ካንፓኒ አስኮም የወርቅ ማዕድን በቢኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የወርቅ ኃብታችንን እያወጣ በእርግጥ ከሆነ የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ በዚሁ ክልል ውስጥ ሆኖ ዜጎች በተለይም አማራዎች የሚታረዱበት የደም መሬት የመሆኑ ሚስጢር ክልሉ በግብፅና ሱዳን የፖለቲካ ሴራ የተጠላለፈ ጣልቃ ገብነት የሚታይበት፣ ሃገራችን እንዳትረጋጋና የተለያዩ የጦር አበጋዞች በመፈልፈል ሽምቅ ተዋጊዎች ንዋሪውን በመግደልና በማፈናቀል ትልቅ በደል ይፈፅማሉ፡፡ በሌላ በኩል የኦዴፒ ብልፅግና መንግሥት ኦሮሙማ የክልሉን ዲሞግራፊ የመቀየር ፕሮግራም መሠረት ያደረገ የአማራ የዘር ማፅዳት በስፋት ሲከናወን ይታያል፡፡ የብልፅግና መንግሥት የክልሉን ደህንነትና ፀጥታ ማስከበር የተሳነው የአማራው ህዝብ መፈናቀልና ስደት ሙሉ በሙሉ እስኪጠናቀቅ ድረስ በመጠባበቅ እንጂ ከአቅሙ በላይ ሆኖ አይደለም፡፡ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ የዘር ማፅዳቱ እንዳለቀ የኦሮሞ ህዝብ ብዛት  በክልሉ ዲሞግራፊ በአስተማማኝ ይቀየራል፣ በዛም ኦሮሙማ እቅድ መሠረት የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ እና የወርቅ ማዕድኑን በመቆጣጠር ኦዴፓ ብልፅግና ኦሮሙማን የመስፋፋት ታክቲክና ስትራቴጂ መፈጸም ይቻለዋል፡፡

የኢዛና  የወርቅ ማእድን የትግራይ ክልል የጦር አበጋዞች መንግሥት የወያኔ ኃብት ነበር፡፡ በተመሳሳይ የለገደንቢ የወርቅ ማእድን የኦሮሞ ክልል የጦር አበጋዞች መንግሥት ኃብት ሆኖል !!! ኢትዮጵያ በአስር ክልል የጦር አበጋዞች መንግሥት የዘር ሠራዊት መስርታ በውስጣዊ ወሰንና ድንበር የጦርነት ግጭቶች በማስተናገድ ላይ ትገኛለች፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ በስቃይ ህይወት ከቀየው በመፈናቀል ኑሮውን የሚገፋበት፣ ህይወቱን ያጣበት፣ ንብረትና ኃብቱ የወደመበት፣ ሴቶች የተደፈሩበት፣ ርሃብና ቸነፈር ያንዣበበት፣  የኮማንድ ፖስት ወታደራዊ አገዛዝ የሰፈነበትና የጦርነት ቀጠና በትግራይና በአማራ ጎንደር በሱዳን ሠራዊት የተወረርንበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡ የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ የኦሮሙማ ሥውር አገዛዝ የወርቅ ማእድን ኃብትን በተመለከተ ፓርላማ አዋጅ አውጥቶል በዚህም መሠረት የወርቅ ኃብቱ የተገኘበት ክልል ተጠቃሚነት 30 በመቶ፣ ለኢንቨስተሩ 60 በመቶ፣  እንዲሁም ወርቁ ተቆፍሮ የተገኘበት ክልል ህዝብ 10 በመቶ የጥቅሙ ተካፋይ እንዲሆኑ አዲስ አዋጅ ወጥቶል፡፡

 

የኢትዮጵያ የወርቅ የውጭ ንግድ ገቢ

  • የወርቅ ማዕድን ኃብት ለሃገራች ኢኮኖሚ ከግብርና ዘርፍ ሌላ አማራጭ በመሆን የሃገሪቱን አማካይ አመታዊ ምርት (ጂዲፒ) አንድ በመቶ ከወርቅ፣ ጂም ስቶንና ታንታለም፣ የኢንዱስትሪ ማዕድናት ወዘተ ለዓለም አቀፍ ንግድ በማቅረብ በ1980 በፊት የማዕድን ኢንዱስትሪ የጂዲፒ አስተዋፅኦ 0.2 በመቶ ነበር፡፡በ2001 እኤአ የወርቅ ማእድን፣ በ2001 እኤአ የውጭ ምንዛሪ ገቢ 5 ሚሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን፣ በ2012 እኤአ 602 ሚሊዮን ዶላር ደርሶ ነበር፡፡
  • በ2013 እኤአ ኢትዮጵያ ከወርቅ ማዕድን ምርት ከውጭ ንግድ ገቢ 419 ሚሊዮን ዶላር ከባህላዊ የወርቅ ማዕድን አምራቾች መገኘቱ ታውቆል፡፡ በዚህም መሠረት 7878.3 ኪሎግራም ከወርቅ ምርት 409.1 ሚሊዮን ዶላር፣ 20126.3 ኪሎግራም ከጂም ስቶን ምርት  3 ሚሊዮን ዶላር፣ እንዲሁም 32.95ቲ ታንታለም 1.6 ሚሊዮን ዶላር፣ የውጭ ምንዛሪ ገቢ ተገኝቶል፡፡ በውጭ ንግድ  የማዕድን ሚኒራልስ ሁለተኛው ትልቁ የውጭ ምንዛሪ ምንጭ ሲሆን  ለሃገሪቱ ጂዲፒ 23 በመቶ አስተዋፅኦ ያደርግ ነበር፡፡
  • በ2014 እኤአ ኢትዮጵያ ከወርቅ ማዕድን ምርት ከውጭ ንግድ ገቢ 445 ሚሊዮን ዶላር ከወርቅ ማዕድን  መገኘቱ ታውቆል፡፡ በ2017 እኤአ መንፈቅ አመት ሃገሪቱ 92 ሚሊዮን ዶላር አግኝታ ነበር፡፡
  • በተመሳሳይ በ2018 እኤአ መንፈቅ አመት ሃገሪቱ 95 በመቶ የወርቅ ማዕድን ኃብት የውጭ ምንዛሪ ገቢዎን አጥታለች፡፡ ሃገሪቱ የውጭ ገቢ ንግድ እቅድ 528 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ የተገኘው 30 ሚሊዮን ዶላር (የእቅዱን አምስት ፐርሰንት ) ብቻ ማግኘቶ ታውቆል፡፡ የሜድሮክ ጎልድ የወርቅ ማዕድን የሃያ አመት ፍቃድ ካለቀ በኃላ በሃገሪቱ በተከሰተው ህዝባዊ አመፅ  ህወሓት/ ወያኔ የትግራይ ክልላዊ መንግስት የኢዛናን የወርቅ ማእድን ሃብትን የግላቸው አድርገው ሲመዘብሩ እስከዛሬ ይገኛል፡፡ “Ethiopia misses 95% minerals’ export target (January 31, 2019) Partly impacted by the revocation of MIDROC Gold license of Ethio-Saudi billionaire Al Amoudi, Ethiopia has missed 95 % of its mining export target for the first six months of the current fiscal year started July 8, 2018. Though the country planned to export different minerals worth $528 million, the country has only got $30 million achieving only 5% of its target, according to the latest report New Business Ethiopia received from the Ministry of trade. The country earned equal amount of hard currency for the same period last year. Meanwhile the target for the first six months last year was $92 million.”
  • በ2019 እኤአ ኢትዮጵያ ከወርቅ ማዕድን ምርት ከውጭ ንግድ ገቢ 32 ሚሊዮን ዶላር ከወርቅ ማዕድን  ገቢ ማሽቆልቆሉ  ታውቆል፡፡ Ethiopia Earnings from Gold Dwindles to just $32M. a record low/ By Staff Reporter/ October 10, 2019 (Ezega.com)

የኦሮሞ ክልላዊ መንግሥት የወርቅ ማእድን ኃብት ኬኛ!!! ፊንፌኔ ኬኛ! ወርቅ ኬኛ!!!

የዶክተር አብይ አህመድ የብልፅግና ፓርቲ የአገር በቀል የኢኮኖሚ አጀንዳ ላይ ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳች መካከል ወርቅን ጨምሮ የማዕድን ዘርፍ ዋነኛዎቹ ሲሆኑ በቀጣይ 3 ዓመታት ውስጥ 3 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ ዕድል ይፈጥራል ተብሎ ታቅዶል፡፡ የኦዴፓ ብልጽግና ፓርቲ መሪ ዶክተር አብይ አህመድ ኢንጅነር ታከለ ኡማን የማዕድን ሚኒስቴር አድርገው ሾመዋል፡፡ የማዕድን ሚኒስቴር በኮቪድ ወረርሽን ጊዜ በአለፈው አምስት ወራቶች ውስጥ 303 ሚሊዮን ዶላር በውጪ ንግድ ገቢ መገኘቱን አብስሮል፡፡ በ2018/19 እኤአ ከተገኘው 49 ሚሊዮን ዶላር ስድስት እጥፍ መገኘቱን ገልፆል፡፡ በ2030 እኤአ የማዕድን ኃብት 17 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ጣቅዶል፡፡   (4)

Ethiopia: Gold mining sees record growth despite Covid-19

Ethiopia generated mining revenue of $303m in the past five months, according to the ministry of mines. That total is more than six times the amount recorded – $49m – in the fiscal year 2018/2019.

It is more than what was earned last fiscal year, which was $207m.

Boom time:-Two years ago, Ethiopia’s gold export earnings were just $27m, down from its historic high performance – at $602m – recorded in 2012.Though coronavirus impacted the East African country’s mining sector, the government raised the price it pays to artisanal miners, who account for more than half of gold production minerals from $265m currently to $17bn by 2030.

Attracting investment:-The government also gives several incentives to investors engaged in the mining sector. This includes a 25% corporate tax rate and permits 10 years’ loss carry-forward, with royalties at 4% for industrial minerals, 5% for metallic minerals and 7% for gold, adding to being exempted from customs duties and taxes on equipment, machinery and vehicles crucial for mining operations.

Ethiopia’s mining potential:-Ethiopia’s mining sector majors in gold, which accounts for over 83% of output. It also produces sapphire, limestone, salt, pumice and tantalum. However, most of the production comes from the informal sector, largely by 350,000 artisanal gold miners, according to the 2017 Ethiopia International Transparency Initiative Report. Ongoing exploration is taking place for gold, with commercially viable discoveries being found.

መደምደሚያ፡- የኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ የኦሮሙማን ፕሮግራም በመላ ኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በውድም በግድም ለመጫን የማያገላብጡት ድንጋይ አይገኝም፡፡  ኦዴፓ ብልፅግና ፓርቲ የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የአብሥራ ዓየር መንገድ እና የለገደንቢና የሌሎች ወርቅ ማዕድናትን በመቆጣጠር ኦሮሙማን የመስፋፋት ታክቲክና ስትራቴጂ በመፈጸም ላይ ይገኛል፡፡ የኦሮሙማ ፕሮግራም አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ደብረ ዘይት፣ ናዝሬት፣ ጂማ፣ አሰላ፣ ሻሸመኔ፣ አጣዬ፣ ደብረብርሃን  ወዘተ ከተሞችን አቃጥሎና አውድሞ ኢትዮጵያን የጀመረችውን የእድገት ጎዳና ማደናቀፍ፣ የግብፅና ሱዳን  የውጪ ጠላቶች ተልኮ የማስፈፀም ተልዕኮ አላቸው፡፡

 

ምንጭ

  • በአዲስ አበባ ዙሪያ በሚገነባው ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የግንባታ ቅድመ ዝግጅት ላይ ውይይት ተካሄደ/ On Feb 17, 2021 አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)
  • Ethiopian Airlines Announces Plans to Build Africa’s Largest Airport (Video)

Ethiopia to Build the Largest Airport in Africa | Travel + Leisure (travelandleisure.com)

(3)    (መጋቢት 24 ቀን 2009 ዓ/ም አዲስ ዘመን ጋዜጣ)

(4)    Ethiopia: Gold mining sees record growth despite Covid-19/By Samuel Getachew,31 December 2020

 

Leave a Reply