ኢትዮጵያ በ2021 ከሁሉም የአፍሪካ ሀገራት ያነሰ እድገት እንደምታስመዘግብ የዓለም የገንዘብ ድርጅት ጥናት አመላከተ፡፡ ዕድገቷም ጠፍጣፋ ዜሮ ነው፡፡ (አሻራ ታህሳስ 28፣ 2013 ዓ.ም) በ…

ኢትዮጵያ በ2021 ከሁሉም የአፍሪካ ሀገራት ያነሰ እድገት እንደምታስመዘግብ የዓለም የገንዘብ ድርጅት ጥናት አመላከተ፡፡ ዕድገቷም ጠፍጣፋ ዜሮ ነው፡፡ (አሻራ ታህሳስ 28፣ 2013 ዓ.ም) በ…

ኢትዮጵያ በ2021 ከሁሉም የአፍሪካ ሀገራት ያነሰ እድገት እንደምታስመዘግብ የዓለም የገንዘብ ድርጅት ጥናት አመላከተ፡፡ ዕድገቷም ጠፍጣፋ ዜሮ ነው፡፡ (አሻራ ታህሳስ 28፣ 2013 ዓ.ም) በኢህአዴግ ዘመን ኢትዮጵያ ባለሁለት አሀዝ ዕድገት በተከታታይነት አስመዘገብኩ ስትል ቆይታለች፡፡ በዓለም የገንዘብ ድርጅት ጥናት መሰረትም ኢትዮጵያ የምትለውን ያህል 11 ከመቶ በየዓመቱ ባታድግም፣ ከዓመት ዓመት ዕድገት እንዳለ ግን አልተካደም፡፡ የለውጥ ጊዜው መጥቶ የዶክተር አብይ አስተዳድር በቆየባቸው ሶስት ዓመታት ውስጥ ግን ዕድገቱ ከኢህአዴግ ዘመኑ እየቀጨጨ ሂዷል፡፡ ለዚህም ህወኃት የኢኮኖሚ ስብራት ስለሰራ እና ለውጡ መንገዱን ስላልጨረሰ ነው የሚል መላምት ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ ብሩ በሙሉ በህወኃት እጅ ነው ያለ በሚል የገንዘብ ኖት ቅየራም ተደርጓል፡፡ የገንዘብ ኖት ቅየራው ግን የህትመት ወጪ ከማውጣት ውጭ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ያመጣው ጠብ የሚል ነገር የለም፡፡ አዲሱ ብር ተመሳስሎ የተሰራው ገና ወር ሳይሞላው ሲሆን፣ ብሩም በኢ- መደበኛ እጆች በመግባቱ የዶላር ዋጋ እስከ 52 ብር እየተመነዘረ ነው፡፡ ሀገሪቱ በመሰረታዊነት የተቋማዊ ውድቀት ስላጋጠማት የገንዘብ ለውጡ ረብ የለሽ ሆኖ ያለፈ ሲሆን፣ የሀገሪቱ ሰላምም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሽቆለቆለ ሂዷል፡፡ የዓለም የገንዘብ ድርጅት ዓለም ከ2020 ው በ2021 በ5.5 ከመቶ ያድጋል፡፡ ሁሉም የአፍሪካ ሀገራትም ከኢትዮጵያ በስተቀር ከ2020 የተሻለ ዕድገት ያስመዘግባሉ ሲል አይ ኤም ኤፍ (IMF) ይፋ አድርጓል፡፡ ከአህጉሩ ኢትዮጵያ ብቻ ከ2020 የተሻለ ምንም አይነት የኢኮኖሚ ዕድገት አይመጣባትም ሲል ትንበያውን አስቀምጧል፡፡ ለትንበያው መሰረት የሆኑትም በሀገሪቱ ግጭት በመበራከቱ የውጭ ባለሀብቶች ለማልማት ባለመግባታቸው እና በማልማት ላይ የነበሩትም እየወጡ በመሆኑ፣ የኮሮና ወረርሽን ያሳደረው ዓለም አቀፍ ተፅዕኖ ፣ የአንበጣ መንጋ ከ200ሺ ሄክታር በላይ ማሳ ማውደሙ 7 ሚሊየን አርሶአደሮች በአንበጣ ምክንያት እርዳታ ጠያቂ መሆናቸው እና ብዙው አርሶአደር በግጭት ምክንያት መፈናቀሉ የኢትዮጵያ ዕድገት ወደ ዜሮ እንዲጠጋ ያደርገዋል ሲል ትንታኔውን አስቀምጧል፡፡ አይ ኤም ኤፍ “ኢትዮጵያ የ2021ክራሞቷ ምንም ከፍታ የሌለው ጠፍጣፋ ዜሮ ነው “ብሏል፡፡ ለአብነት እንኳን ለምለም የሚባሉት የሁመራ፣ የመተከል እና የወለጋ አርሶአደሮች ምርታቸውን በግጭት ምክንያት አልሰበሰቡም፡፡ በዚያ ላይ የኢትዮጵያ መንግስት የተበላሸ የአመራር ሂደት በመከተሉ ዲፕሎማሲው ስለተበላሸበት ዓለምአቀፍ ድጎማው እየተቀነሰበት ነው፡፡ የአውሮፓ ህብረት እና አሜሪካ ለኢትዮጵያ የሚሰጡትን ድጋፍ በከፊል አቋርጠዋል፡፡ ከሱዳን፣ ከሶማሊያ እና ከጅቡቲ ጋር ያለው ግንኙነትም የሰመረ ስላልሆነ ንግዱን ለማሳለጥ አንድ ማነቆ የሆነ ሲሆን፣ በአንፃሩ ወደ ኢትዮጵያ የሚገባው ህገወጥ የጦር መሳሪያ በዝቷል፡፡ ሀገሪቱ ለመድሃኒት መግዣ እየተቸገረች እንደሆነ አሻራ ያረጋገጠ ሲሆን፣ በዶላር መደበኛ ባልሆነ ሁኔታ እየተገዛ የሚገባው ዘመናዊ መሳሪያ እየበዛ ሂዷል፡፡ ኢ- መደበኛ ታጣቂዎች የመንግስትን ሀይል እየተገዳደሩትም ይገኛሉ፡፡ በአብይ አህመድ የሚመራው መንግስት የተረኝነት ስሜት አግላይነትን በመፍጠሩ የሀገር ውስጥ ባለሀብቶችም የስራ ያላቸው ተነሳሽነት እየወረደ እንደሆነ በምሬት ይናገራሉ፡፡ በኦሮሚያ ክልል የበርካታ ባለሀብቶች ንብረት የወደመ ሲሆን፣ የተረፈላቸውንም በኢ-መደበኛ ቡድኖች ገንዘብ ስጡን በማለት ባለሀብቶች እየተሳቀቁ ነው፡፡ የተዛባው የፍትህ ስራዓትም ባለሀብቶችን የፖለቲካ ስጋት እንዳይሆኑ በሚል እያደናቸው ይገኛል፡፡ በአንፃሩ በአንድ ዓመት ውስጥ ባጫ ጊና 40 ቢሊየን ብር ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያላግባብ ሲመዘበር ተጠያቂ እንዳይሇን ወደ ውጭ በአምባሳደርነት ተሸኝቷል፡፡ የሀገሪቱን 60 ከመቶ ገበያ የያዘው ንግድ ባንክ በተረኝነት ስሜት እየኮሰሰ ሲገኝ፣ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ የሚመሩት አምባሳደር ግርማ ብሩም የተረኝነት ወኪል ሆነው ቤተመንግስት እንደገቡ አሻራ በተደጋጋሚ አስነብቧል፡፡ በአንፃሩ ቡና ፣ አቢሲኒያ፣ ወጋገን .. .የመሳሰሉትን ባንኮች ለማክሰር በተለይም የቡና እና የአቢሲኒያ ፕሬዜዳንቶች ያላግባብ እንደተከሰሱ አሻራ ሰምቷል፡፡ በጠቅላላው በሀገሪቱ ተቋማት ላይ ለመትከል የታሰበው የተረኝነት መንፈስ ፣ ግጭቶች ፣የአንበጣ መንጋ እና ሌሎች ሰው ሰራሽ እና ተፈጥሮአዊ ምክንያቶች ተዳምረው የኢትዮጵያ ዕድገት ቁልቁል እንዲጓዝ ያደርጋል፡፡ ኢትዮጵያ ከለውጡ ወዲህ እንኳን 700ቢሊየን ብር አካባቢ ዕዳ የገባች ሲሆን፣ አጠቃላይ አሁን ያለባት ዕዳ ከሁለት ትሪሊየን ብር በላይ ደርሷል፡፡ ይህ ማለት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በነፍስ ወከፍ 21ሺ ብር ብድር ገብቷል እንደማለት ነው፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply