ኢትዮጵያ በ2021 – የቀጠሮ ግጭት (አሻራ ታህሳስ 24 ፣ 2013 ዓ.ም) ዓለም አቀፍ የግጭት ትንተና ቡድን በ2021 በዓለማችን የግጭት ምድር ይሆናሉ ካላቸው ሀገራት መካከል ኢትዮጵያን…

ኢትዮጵያ በ2021 – የቀጠሮ ግጭት (አሻራ ታህሳስ 24 ፣ 2013 ዓ.ም) ዓለም አቀፍ የግጭት ትንተና ቡድን በ2021 በዓለማችን የግጭት ምድር ይሆናሉ ካላቸው ሀገራት መካከል ኢትዮጵያን ከአፍጋኒስታን ቀጥሎ ስሟን ጠቅሷታል፡፡ የትንተና ቡድኑ ይሄን ያለበት ምክንያት ሲያስቀምጥም የሚከተሉትን ሀሳቦች አስፍሯል፡፡ 1) የህወኃት ጉዳይ የተራዘመ ጦርነትን ይዞ ይመጣል፡፡ የኩርፊያ ቡድኖች የሽምቅ ጥቃት ሊፈፀሙ ይችላሉ፡፡ የህወኃት አመለካከት ደጋፊዎች መኖራቸው እና ይሄንም ለማስታረቅ አለመቻሉ የቀጠሮ ግጭት እንዲነሳ ሊያደርግ ይችላል፡፡ 2) ዶክተር አብይ ሀገሪቱ የምትመራበትን ዘላቂ እና አካታች ስራዓተመንግስት ማዋቀር አለመቻላቸው ነገን በግጭት እንዲጠበቅ አድርጎታል፡፡ 3) የኦሮሞ ፖለቲከኞች በገዥው መንግስት ስር የሰደደ ኩርፊያ እና ይሄንንም ለማስከን የሚወሰደው እርምጃ ዝቅተኛ መሆኑ 4) የአማራዎች መፈናቀል እና በጠላትነት የፈረጀ ፖለቲካ መኖሩ በሀገሪቱ በቀጣይ ዓመት ሰላም ላይኖር ይችላል ብሏል፡ 5) በብሄረሰቦች መካከል ያለው ጥላቻ እያደገ መሄዱ እና ሽኩቻው በዝቶ የጠረጴዛ ፖለቲካ ማብቃቱ እና በየአካባቢው ኢ- መደበኛ ታጣቂዎች የመንግስትን ሀይል መገዳደራቸው የቀጠሮ ግጭት እንዳለ አመላካች ሆኗል፡፡ 6) የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና በሀይማኖት እና በብሄር ግጭት ምክንያት የተረጋጋ ፖለቲካ የለውም፡፡ ይህም ቀጠናዊ ብጥብጥን ሊፈጥር መቻሉ ኢትዮጵያን አጣብቂኝ ውስጥ ሊከታት ይችላል፡፡ 7) በበረሃ አንበጣ፣ በጎርፍ፣በመፈናቀል እና ጦርነት አርሶአደሩ ምርቱን መሰብሰብ ባለመቻሉ እንዲሁም ከኮሮና ተፅዕኖ ጋር ተዳምሮ በኢትዮጵያ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ውድቀት ያጋጥማል፡፡ የኑሮ ውድነቱ እና የስራ ዕድል መጥፋት ከብሄር ተቃርኖው ጋር ተነባብሮ ኢትዮጵያ የዓለማችን የ2021 የግጭት ማዕከል ትሆናለች የሚል ትንተና ወጥቷል፡፡ ቅድመ ግምት ስለሆነ አካታች የፖለቲካ ውይይቶች፣ ነፃ እና ገለልተኛ ተቋማት ከተፈጠሩ፣ የዜግነት መብት ከተረጋገጠ፣ የህግ የበላይነትነን ማስፈን ከተቻለ ግን ስጋቱ ስጋት ብቻ ሆኖ ሊቀር ይችላል፡፡ ለዚህም አስፈላጊ ትንተና እና መፍትሄ ሰርቶ መጠበቅ ከሁሉም የሚጠበቅ ሀላፊነት ይሆናል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply