ኢትዮጵያ ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ ከቡና ሽያጭ ከ184 ሚለዮን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች።በያዝነው ዓመት ማለትም ባለፊት ሶስት ወራት ውስጥ 80 ሺ ቶን ቡና ለዓለም ገበያ ለመላክ ታቅዶ 53…

ኢትዮጵያ ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ ከቡና ሽያጭ ከ184 ሚለዮን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች።

በያዝነው ዓመት ማለትም ባለፊት ሶስት ወራት ውስጥ 80 ሺ ቶን ቡና ለዓለም ገበያ ለመላክ ታቅዶ 53 ሺ ቶን በላይ ቡና ወደ ውጪ አገራት ተልኳል።

በዚህም ከ184 ሚለዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የኢትዮጲያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

የኢትዮጲያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ም/ዋና ዳሬክተርና የግብይት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ሻፊ ኡመር ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቁት በሩብ ዓመቱ ቡናን ወደ ውጪ በመላክ የተገኘው ገቢ በባፈው ዓመት በአጠቃላይ ተጠናቆ ያልተላከውን ቡና አጠናቆ በመላክ ነው፡፡

የ2013 ዓ.ም ያልታጠበ ቡና እየተሰበሰበ ነው ያሉን ሲሆን ይሄንን ምርት አሰባስቦ ወደ ገበያ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን ነግረውናል፡፡

በዓመቱ 3 መቶ 12 ሺ ቶን ቡና ወደ ውጪ በመላክም ከ1 ቢለየን በላይ ዶላር ገቢ ለማግኘት መታቀዱን ከባለስልጣኑ ሰምተናል፡፡

በባለፈው ዓመት አንድ ቶን ቡና 2 ሺ 833 ዶላር ሲሸጥ እንደነበር አስታውሰው በዘንድሮ ሩብ ዓመት ይህንን በማሻሻል በሩብ ዓመቱ አንድ ቶን ቡና 3 ሺ457 ዶላር እየተሸጠ መሆኑንን ነግረውናል፡፡

በተመሳሳይ የ 2011 ዓ.ም ምርቱ በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ዓለም ገበያ የቀረበበት ዓመት እንደሆነ ያነሱት አቶ ሻፊ የቡና ምርቱ ለዓለም ገበያ ቀርቦ ከፍተኛ ገቢ አስገኝቶ ነበር።

የዉልሰዉ ገዝሙ
ጥቅምት 19 ቀን 2013 ዓ.ም

Source: Link to the Post

Leave a Reply