ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር ነች አንድ ሚልዮን ወታደር ሊኖራት ይገባል። ወጣቶች 12ኛ ክፍል እንደጨረሱ ለስድስት ወራት የብሄራዊ ውትድርና አገልግሎት ቢሰጡ ይጠቀማሉ።መጪው አዲሱ ፓርላማ በፍጥነት ተወያይቶ መወሰን ያለበት ቀዳሚ አጀንዳ መሆን አለበት።

ከአጭር ፅሁፉ ስር ከ800 ሰው በላይ የተሳተፈበት ኢትዮጵያዬ የተሰኘው አዲስ ዜማ ያገኛሉ።ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር ነች።ከ115 ሚልዮን በላይ ለሆነው ህዝቧ እና የእንግሊዝን መሬት አራት ጊዜ ለሚበልጥ መሬቷ አንድ ሚልዮን ሰራዊት ያስፈልጋታል።ይህ ሰራዊት በሰላም ጊዜ ያመርታል።በጦርነት ጊዜ የሀገር ሰላም ያስከብራል።ሰራዊቱ የሀገር ሸክም አይሆንም።የራሱ ግዙፍ ዘመናዊ የእርሻ ቦታዎች፣ዘመናዊ ፋብሪካዎች እና በመከላከያ ስር ያሉ ሌሎች የልማት ድርጅቶች ሊኖሩት ይችላሉ።በመሆኑም ሰራዊቱ በሰላም ጊዜ የመንግስት በጀት የሚበላ ሳይሆን ራሱን በራሱ የሚያግዝ ይሆናል።በሌላ በኩል ወጣቶች 12ኛ ክፍል እንደጨረሱ ለስድስት ወራት የብሔራዊ

Source: Link to the Post

Leave a Reply