ኢትዮጵያ አረንጓዴ አሻራን ለጎረቤት ሀገራት  ልታጋራ ነው፡፡

የአረንጓዴ አሻራን ልምድ በማጋራት እና መልካም ተሞክሮን ከማስፋፋት አንጻር አረንጓዴ ዲፕሎማሲ በሚል እየተሰራ እንደሚገኝ እና ለዚህ አለማ የሚውልም 1 ቢሊየን ችግኞችን አንደምትሰጥ በአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ጋሻው ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

ችግኞቹ እንደየሀገራቱ መልከዓ ምድራዊ ሁኔታ አፍልቶ ለመስጠት እንደተሰራ ገልጸዋል፡፡ችግኝ የማፍላት ስራው መጀመሩን የጠቀሱት አቶ ተስፋዬ ክልሎች በልዩ ቦታ ላይ የሚተክሉትን ዓይነት እና ቦታ በመለየት እየሰሩ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡

በተለይም ወደ ጎረቤት ሀገራት የሚላኩት ችግኞች ከስድስት የተመረጡ ክልሎች እና ከስምንት ዩኒቨርስቲዎች ጋር በጋራ ለመስራት በሳይንሳዊ ጥናት እየተደረገ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡

*****************************************************************************

ዘጋቢ፡እየሩሳሌም ብርሃኑ

ቀን 21/04/2013

Source: Link to the Post

Leave a Reply