You are currently viewing ኢትዮጵያ አራት የአየርላንድ ዲፕሎማቶችን በአንድ ሳምንት ውስጥ ከሀገር ለቀው እንዲወጡ አዘዘች።  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ     ህዳር 15 ቀን 2014 ዓ.ም         አዲስ አበባ ሸዋ…

ኢትዮጵያ አራት የአየርላንድ ዲፕሎማቶችን በአንድ ሳምንት ውስጥ ከሀገር ለቀው እንዲወጡ አዘዘች። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 15 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ…

ኢትዮጵያ አራት የአየርላንድ ዲፕሎማቶችን በአንድ ሳምንት ውስጥ ከሀገር ለቀው እንዲወጡ አዘዘች። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 15 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በአዲስ አበባ አየርላንድ ኤምባሲ እየሰሩ ካሉት 6 ዲፕሎማቶች መካከል 4 የሚሆኑት በሳምንት ውስጥ ከሀገር ለቀው እንዲወጡ መወሰኗን ኢትዮጵያ አስታውቃለች፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ለአል ዐይን አማርኛ እንዳሉት በኢትዮጵያ ይሰሩ የነበሩ አራት የአየርላንድ ዲፕሎማቶች በሳምንት ውስጥ ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ መወሰኑን ገልጸዋል ያለው አል ዐይን ነው፡፡ የአየርላንድ አምባሳደር እና አንድ ሌላ ዲፕሎማት መቆየት እንደሚችሉም ተገልጧል። የአይሪሽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሞን ኮቨኔይ “በዚህ የኢትዮጵያ መንግስት ውሳኔ በጣም አዝኛለሁ” በማለት ርምጃው ጊዜያዊ እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ ስለማለታቸው ኤፍፒ ዘግቧል። ዲፕሎማቶቹ አገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የታዘዘውም አየርላንድ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት አስመልክቶ በወሰደች አቋም ምክንያት ስለመሆኑ ገልጧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply