ኢትዮጵያ አዲስ የገንዘብ ዓይነቶችን መጠቀም ልትጀምር መሆኗ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 4 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ኢትዮጵያ ነባሮቹን የ…

ኢትዮጵያ አዲስ የገንዘብ ዓይነቶችን መጠቀም ልትጀምር መሆኗ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 4 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ኢትዮጵያ ነባሮቹን የ10፣ የ50 እና የ100 ብር የገንዘብ ዓይነቶች ሙሉ ለሙሉ በመተካት ለግብይት የሚሆን አዲስ የገንዘብ ዓይነት መጠቀም እንደምትጀምር በዛሬው ዕለት ተገልጧል። ይህም አዲሱን የ200 ብር ገንዘብ አይነትን መጠቀምን የሚጨምር ሲሆን አዲስ የገንዘብ ዓይነቶችም በርካታ ጥቅም እንዳላቸው ተነግሯል። በዋናነትም ለሕገ ወጥ እንቅስቃሴዎች የሚደረግን ድጋፍ፣ ሙስናን እና የኮንትሮባንድ ሥራዎችን ለመቀልበስ እንደሚረዱ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በይፋዊ የፌስ ቡክ ገጻቸው ያሰፈሩት። በአዲሶቹ የገንዘብ ዓይነቶች ላይም የተካተቱ መለያዎች አመሳስሎ ገንዘብ ለማተም የሚደረጉ ሕገ ወጥ ጥረቶችንም ለማስቀረት ያግዛሉ ነው የተባለው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply