ማክሰኞ ሰኔ 28 ቀን 2014 (አዲስ ማለዳ) ኢትዮጵያ እና ሱዳን በመካከላቸው ያሉ ያልተፈቱ ቀዳሚ ጉዳዮቻቸውን በሰላማዊ መንገድ በውይይት ለመፍታት ቁርጠኝነታችንን ገልጸናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ።
በ39ኛው የኢጋድ መሪዎች አስቸኳይ ጉባኤ ለመሳተፍ ኬንያ፤ ናይሮቢ የሚገኙት የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከጄኔራል አብዱል ፈታሕ አል-ቡርሃን ጋር ውይይት አድርገዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውይይቱን ተከትሎ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት “ኹለቱ አገራት በሰላማዊ መንገድ ሊሠሩባቸው የሚችሉ በርካታ የትብብር መሠረቶች እንዳሏቸው አረጋግጠናል ” ብለዋል።
“ያለን ትሥሥር ከየትኛውም መከፋፈል የሚበልጥ ነው ” ያሉት ዶ/ር ዐቢይ ” ኹለታችንም ያልተፈቱ ቀዳሚ ጉዳዮችን በሰላማዊ መንገድ በውይይት ለመፍታት ቁርጠኝነታችንን ገልጸናል” ሲሉ አሳውቀዋል።
Source: Link to the Post