ኢትዮጵያ እና ሱዳን የድንበር ውዝግባቸውን ለመፍታት ነገ ማክሰኞ ድርድር እንደሚጀምሩ የሱዳኑ ጠቅላይ ምኒስትር አብደላ ሐምዶክ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ   ታህሳስ 1…

ኢትዮጵያ እና ሱዳን የድንበር ውዝግባቸውን ለመፍታት ነገ ማክሰኞ ድርድር እንደሚጀምሩ የሱዳኑ ጠቅላይ ምኒስትር አብደላ ሐምዶክ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 1…

ኢትዮጵያ እና ሱዳን የድንበር ውዝግባቸውን ለመፍታት ነገ ማክሰኞ ድርድር እንደሚጀምሩ የሱዳኑ ጠቅላይ ምኒስትር አብደላ ሐምዶክ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አማሚ ታህሳስ 12 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የሱዳን ጠቅላይ ምኒስትር ጽሕፈት ቤት ባወጣው መግለጫ እንዳለው፦ ሐምዶክ እና የኢትዮጵያ አቻቸው ዐቢይ አሕመድ ትናንት እሁድ ተገናኝተው ማክሰኞ ታኅሣስ 13 ቀን 2013 ዓ.ም የሁለቱን አገሮች ድንበር ለማካለል የተቋቋመው ኮሚቴ በሚያደርገው ድርድር ላይ ተወያይተዋል። ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሱዳኑ አቻቸው አብደላ ሐምዶክ የተነጋገሩት በጅቡቲ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት (ኢጋድ) አስቸኳይ ስብሰባ በሚደረግበት ነው። ሁለቱ አገራት በድንበር ጉዳይ ለመጨረሻ ጊዜ የተነጋገሩት ባለፈው ግንቦት እንደነበር ያስታወሰው የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት ለሰኔ የተቀጠረው ቀጣይ ውይይት መሰረዙን ዘግቧል። ኢትዮጵያ እና ሱዳን 1,600 ኪሎ ሜትር የሚረዝም ድንበር ይጋራሉ። የሱዳን መንግሥት የሚቆጣጠረው ሱና የዜና ወኪል ባለፈው ሳምንት ግጭት ወደ ተቀሰቀሰበት አል-ፋሻጋ የተባለ አዋሳኝ አካባቢ አገሪቱ ጦሯን እንዳሰማራች ዘግቧል። የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀ-መንበር ሌቴናንት ጄኔራል አብዱል ፋታኅ አል-ቡርኻን ግጭቱ ወደ ተቀሰቀሰበት የድንበር አካባቢ አቅንተው ለሦስት ቀናት ቆይታ አድርገዋል። በሁለቱ አገሮች ድንበር ግጭት መፈጠሩ ከተሰማ በኋላ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ «ሁልጊዜም ልዩነቶቻችንን በውይይት ስለምንፈታ እንዲህ አይነት ኩነቶች የሁለቱን አገሮች ትስስር አይሰብሩም» የሚል መልእክት በማኅበራዊ መገናኛ ገጾቻቸው አስተላልፈዋል ሲል ኢትዮ ኒውስ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply