ኢትዮጵያ እና ሱዳን ያለባቸውን የድንበር ዉዝግብ ለመፍታት ለመስራት ተስማምተዋል፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እና የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አብዱልፈታ አልቡርሃን የሁለ…

https://cdn4.telegram-cdn.org/file/pWlnHx6REguGYl97Lh-frIRoPmdCZ72qxR7w5RRBnuHbEM0t7Cg4PbPQJxQPxw3TfnXldAy8hB00RiE7QHv1BQ6xCJMdxcTAPx6sE3eEegrdEkDheWWYexNn3W0c8NC0R1hFgz2PzNVQOYHmTM826FqjYky-A2vIri0lprWOsQGVCIVTt81VBq_CT_YN33SrodXN6DH6KzNU3QOO_ASQ4hxehMFiJxxQnKVSl8oZRt4GLRnTKb8FXx_eAVmDDE8wpn5XkuU6T1m_pMexiIK4rFaNaN3iUMemaUBkjA11eNIpJSclnLAwkSiaeaA6qozS5cNkvNsooO5lIVU0OQf1zg.jpg

ኢትዮጵያ እና ሱዳን ያለባቸውን የድንበር ዉዝግብ ለመፍታት ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እና የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አብዱልፈታ አልቡርሃን የሁለቱን አገራት የድንበር ዉዝግብ ችግር የመፍታት ስራዎችን ለማፋጠን መስማማታቸዉ ተገልጿል፡፡

መሪዎቹ በትናንትናዉ ዕለት የድንበር ዉዝግብን በመፍታት እና ኢኮኖሚያዊ ትብብርን በማጠናከር ላይ ያለመ ዉይይት ማድረጋቸዉን አናዶሉ ዘግቧል፡፡

መግለጫዉ ሁለቱ አገራት በጋራ ግንኙነት እና ተባብሮ መስራት ላይ እንዲሁም የጋራ የሆኑ ቀጣናዊ እና ዓለምዓቀፋዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል ብሏል፡፡

በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ በቅርቡ ሱዳንን በጎበኙበት ወቅት መስማማት ላይ የተደረሰባቸዉን ጉዳዮች ማስፈጸም ላይ መነጋገገራቸዉ ተገልጿል፡፡

ባለፉት ዓመታት የኢትዮጵያ እና ሱዳን ግንኙነት በታላቁ ህዳሴ ግድብ እና በድንበር ዉዝግብ ምክንያት ዉጥረት ነግሶበት እንደነበር የሚታወስ ነዉ፡፡

በእስከዳር ግርማ

የካቲት 28 ቀን 2015 ዓ.ም

ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራምና የዩቲዩብ ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ!

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast

ያሎትን አስተያየት እና ጥያቄ በአጭር መልዕክት 6321 ላይ ይላኩልን።
ከኛ ጋር ስለሆናችሁ ከልብ እናመሰግናለን።

Source: Link to the Post

Leave a Reply