ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ኅብረት የሳሞአ ሥምምነት እንድትወጣ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠየቀየኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት የበላይ ጠባቂ አባቶች ህዳር 2016 ዓ. ም የተወሰኑ የአፍሪካ፣ የካሪቢያን…

ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ኅብረት የሳሞአ ሥምምነት እንድትወጣ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠየቀ

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት የበላይ ጠባቂ አባቶች ህዳር 2016 ዓ. ም የተወሰኑ የአፍሪካ፣ የካሪቢያንና የፓሲፊክ ሀገራት የንግድና የኢኮኖሚ አሳሪ የአጋርነት ስምምነትን ከአውሮፓ ኅብረት ጋራ “የሳሞአ ስምምነት“ መፈራረማቸውንና ኢትዮጵያ አንዷ ፈራሚ መሆኗን ጠቅሰው ኢትዮጵያ ራሷን ከስምምነቱ እንድታገል ጠይቀዋል።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሀገርን እጅግ የሚጎዱ  አንቀጾች የተካተቱበት እና “ለሀገራችን ሕዝብ ዕድገትን ሳይሆን ውድቀትን፣ ከፍተኛ የሞራል ዝቅጠትን የሚያስከትል፣  የሀገሪቱን ሉዓላዊነት አደጋ ላይ የሚጥል” ያለውና መንግሥት ፈርሞታል ካለው አለም አቀፍ ስምምነት እንዲወጣ ጠየቀ። 

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት የበላይ ጠባቂ አባቶች ህዳር 2016 ዓ. ም ኢትዮጵያን ጨምሮ የተወሰኑ የአፍሪካ፣ የካሪቢያንና የፓሲፊክ ሀገራት ተፈራረሙት ካለው ስምምነት ኢትዮጵያ ራሷን እንድታገል፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም ስምምነቱን ባለማጽደቅ አደራውን እንዲወጣ ሲሉ ጠይቀዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር “የኢትዮጵያ መንግሥት እንደዚህ አይነት ሥምምነት አፀድቃለሁ ብሎ አልፈረመም።” በማለት ጉባኤው “የተሳሳተ መረጃ ” እንዳለው ገልጿል።

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት የበላይ ጠባቂ አባቶች ህዳር 2016 ዓ. ም የተወሰኑ የአፍሪካ፣ የካሪቢያንና የፓሲፊክ ሀገራት ለሚቀጥሉት 20 ዓመታት ጸንቶ የሚቆይ የንግድና የኢኮኖሚ አሳሪ የአጋርነት ስምምነትን ከአውሮፓ ኅብረት ጋራ “የሳሞአ ስምምነት“ መፈራረማቸውንና ኢትዮጵያ አንዷ ፈራሚ መሆኗን ጠቅሰው ኢትዮጵያ ራሷን ከስምምነቱ እንድታገል ጠይቀዋል። 

የካቲት 05 ቀን 2016 ዓ.ም

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ወቅታዊ አዳዲስ መረጃዎችና ፕሮግራሞችን ለማግኘት ከታች ያሉትን ገፆቻንን ይጎብኙ ቤተሰብ ይሁኑ ።

Telegram https://t.me/ethiofm107dot8

Twitter https://twitter.com/EthioFM

YouTube https://www.youtube.com/@onelovebroadcast/videos

Facebook  https://www.facebook.com/onelovebroadcast

Website https://ethiofm107.com/

Source: Link to the Post

Leave a Reply